የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በክልሉ የመጀመሪያ፣እጅግ ዘመናዊና የተራቀቁ የምርመራ መሳሪያዎችን በቅርብ አስገብቶ ሥራ እንደሚያስጀምር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕ…

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በክልሉ የመጀመሪያ፣እጅግ ዘመናዊና የተራቀቁ የምርመራ መሳሪያዎችን በቅርብ አስገብቶ ሥራ እንደሚያስጀምር አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 8 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በክልሉ የመጀመሪያ የሆኑ እጅግ ዘመናዊና የተራቀቁ የምርመራ መሳሪያዎችን በቅርብ አስገብቶ ሥራ እንደሚያጀምር አብስሯል። ሥራ ከሚጀምሩት መሳሪያዎች መካከልም ኤም አር አይ ስካነር፣ሲቲ ስካን፣ አድባንስድ ስሪ ዲ እና ማሞ ግራፊ የተሰኙት ይገኙበታል። እነዚህ የመመርመሪያ መሳሪያዎችም በተለይም (3T MRI and 128-Slice CT) በሀገራችን በብዛት የማይገኙ በመሆናቸው የሆስፒታሉን የሕክምና አገልግሎትንና የትምህርት ጥራትን ከማሻሻል ባሻገር የሪፈራል ማዕከል በመሆን የሌሎችን የጤና ተቋማት ችግር ለመፍታትም ከፍተኛ እገዛ ያደርጋሉ ተብሏል። ላለፉት ሁለት ዓመት ሆስፒታሉ እነዚህን መሳሪያዎች እንዲያሟላ ሲጠይቅ ለነበረው ታካሚም ታላቅ እፎይታ ስለመሆኑ ሆስፒታሉ አስታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ በመጠናቀቅ ላይ ያለው በሀገራችን በግዝፈቱ ሁለተኛ የሆነው የሕክምና ኦክስጅን ማምረቻ ሥራ ሲጀመር ከ550 በላይ የህሙማን አልጋዎች ከማዕከላዊ ማሰራጫ በተዘረጉ ቱቦዎች (ያለ ሲሊንደር ) ወደተለያዩ ክፍሎች በቀጥታ ማቅረብ ያስችለዋል ተብሏል። ለሌሎች ተቋማትም የሕክምና ኦክስጅን በሲሊንደር እየሞላ የማከፋፈል አቅም ስለሚኖረው በባሕር ዳር ከተማና በአካባቢዉ በሚገኙ የጤና ተቋማት የሚታየውን የህክምና ኦክስጅን እጥረት በዘላቂነት እንደሚፈታ ተጠቁሟል። የሕክምና ክፍሎቻችን ዉብና ማራኪ ይሆኑ ዘንድ ማገዝ ለሚፈልጉ ግለሰቦችና ባለሀሃብቶችም በሩን ክፍት አድርጎ እንደሚጠብቅ ያስታወቀው ጥበበ ግዮን ከፍ ያለ አስተዋጽኦ ለሚያደርጉ ወገኖች በስማቸው ሆስፒታሉ ዉስጥ ዘላቂ ማስታወሻ እንዲኖር እናደርጋለን ብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply