የባቢሌ ዝሆኖችን የመጠለያ ችግር ለመፍታት ከመንግስት ፈጣን ምላሽ ማግኘት አልተቻለም ተባለ፡፡

የአካባቢ ደን እና ዱር እንስሳ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ሀላፊ አቶ ኩመራ ዋቅጅራ የባቢሌ ዝሆኖችን የመጠለያ ችግር ለመፍታት ከመንግስት ፈጣን ምላሽ ማግኘት እንዳልተቻለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

በሶማሌና ኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ቦታ ላይ የሚገኘውን የባቢሌን የዝሆኖች መጠለያ ችግር ለመፍታተት ለመንግስት ጥያቄ ቢቀርብም የሚመለሰው ምላሽ አጥጋቢ አንዳልሆነ ተነግሯልል፡

በአካባቢዉ ያለው ጸጥታ ግጭትና አለመረጋጋት ለባቢሌ መጠለያ ጣቢዎች ላለው ህገወጥ ሰፈራ ትልቁ ምክንያት እንደሆነ አቶ ኩመራ አስታወቋል፡፡

ፖለቲካዊ ውሳኔዎች መጠበቃቸው ችግሩን ለመቅረፍ አለማሰቻሉንም ተናገረዋል፡፡

በዝሆኖች መጠለያ ጣቢያ ውስጥ በተደረገው ህገወጥ ሰፈራ ዝሆኖች የሚኖሩበትና የሚራቡበት ቦታ በእርሻ፣ በከሰል ምርት፣ በመንገድና መኖሪያ ቤት ግንባታ ደን እየመነመነ በመምጣቱ ዝሆኖቹ ላይ የመጥፋት አደጋ ናቸዉ ተብሏል፡፡

መንግስት ጉዳዩን በቸልተኝነት እያየዉ እንደሆነም ተነስቷል፡፡

አቶ ኩመራ ዋቅጅራ እንደሚሉት ፤ ከሁለቱም ክልሎች በተስፋፋ ህገወጥ ሰፈራ ምክንያት መጠለያው ውስጥ በሰፈሩ የማህበረሰብ ክፍሎችና በዝሆኖች መካከል የመኖርና አለመኖር ግጭት ተፈጥሯል ብለዋል፡፡
ችግሩን መነግስት እንደፈታልን ደጋግመን ጥሪ በማቅረብ ላይ ነን ሲሉ አቶ ኩመራ አንስተዋል።

በመጠለያ ጣቢያ ውስጥ የሰፈሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በበቀል ስሜትና ለኢኮኖሚ ጠቀሜታ ሲባል በህገወጥ አደን ዝሆኖች እየተገደሉ ችግሩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

ባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ 6 መቶ ዝሆኖችን ይዞ በ1962 ቢቋቋምም በአሁኑ ጊዜ ከ 3 መቶ የማይበልጡ ዝሆኖች እንደሚገኙበት ይነገራል፡፡

በለአለም አሰፋ

የካቲት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply