የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ችግር አሁንም መፍትሔ አላገኘም ተባለ፡፡የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እና የኦሮሚያ ክልል መንግስትን ሲያወዛግብ የነበረዉ የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ…

የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ችግር አሁንም መፍትሔ አላገኘም ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለስልጣን እና የኦሮሚያ ክልል መንግስትን ሲያወዛግብ የነበረዉ የባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ፓርክ ጉዳይ ላይ አወንታዊ የመፍትሄ ሃሳብ ቢኖርም መሬት ላይ የወረደ ነገር እንደሌለ ሰምተናል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ሀላፊ አቶ ኩመራ ዋቅጅራ ለጣቢያችን እንደገለፁት የስምምነት ሂደቶች መኖራቸውን ቢያምኑም መሬት ላይ የወረደ ነገር የለም ብለዋል።

የፓርኩ መጠለያ ለኢንቨስተሮች ተሰጥቶ የነበረ ሲሆን ባለስልጣኑና የክልሉ መንግስት ባለሀብቶቹ ከያዙት መሬት ይልቀቁ አይለቁም በሚለዉ ጉዳይ ውዝግብ መፈጠሩ የሚታወስ ነው፡፡

ሁለት አካላት በጉዳዩ ላይ አደረጉት በተባለዉ ውይይት ባለሀብቶቹ ይዘዉት የነበረዉን ስፍራ ለቀዉ እንዲወጡ ተወስኗል ተብሎ የሚሰራጨው መረጃ ገና እና ጊዜ የሚፈልግ እንደሆነ ባለስልጣኑ ለጣቢያችን ተናግሯል።

ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍ ኤም የዱር እንስሳት እና ጥበቃ ባለስልጣን ከዚህ ቀደም የባቢሌ ዝሆኖችን የመጠለያ ችግር ለመፍታት ከመንግስት ፈጣን ምላሽ ማግኘት እንዳልቻለ መዘገባችን የሚታወስ ነው።

በለአለም አሰፋ

መጋቢት 23 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply