የባክሙት ጦርነት አብቅቷል—ፑቲን

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የምስራቅ ዩክሬይን ከተማ የሆነችው ባክሙት ነፃ መውጣቷን ገልፀዋል።

“ለከተማዋ ነፃ መውጣት የድርሻችሁን የተወጣችሁ የሩሲያ ወታደሮች እና የዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊዎችን እንኳን ደስ አላችሁ፣ለስራችሁም እናመሠግናለን” ብለዋል።

በክሬምሊን ድህረገጽ ላይ የወጣው መግለጫ፣ለ15 ወራት ሲካሄድ የነበረው ረጅሙ እና ደም አፋሳሹ ጦርነት በሩሲያ አሸናፊነት ተጠናቋል፤ በሞስኮ ወገን ለነበሩ እና ጦርነቱን እንድናሸንፍ እገዛ ላደረጉ በሙሉ የብሄራዊ ሜዳይ የሚሰጣቸው ይሆናል ይላል።

መግለጫው አክሎም ባክሙት ነፃ እንድትወጣ የተዋጉ የዋግነር ቅጥረኛ ተዋጊዎች እና እነሱን አስፈላጊ በሆነ መሳሪያ ሁሉ ሲረዱ እና አብረው ሲዋጉ የነበሩ የሩሲያ ወታደሮችን አመስግኖ ሁሉም ብሄራዊ የክብር ሜዳይ የሚያገኙ ይሆናል ማለቱን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ግንቦት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply