የቤሩቱ ወደብ ፍንዳታ ታሳሪዎች እንዲፈቱ የሊባኖስ ከፍተኛ አቃቤ ሕግ አዘዙ

https://gdb.voanews.com/800f0000-c0a8-0242-d355-08daff7ba7bc_w800_h450.jpg

የሊባኖሱ ከፍተኛ አቃቤ ህግ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2020 በቤሩት ወደብ ላይ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ በተደረገው ምርመራ በወንጀል ተጠርጥረው የተያዙት ታሳሪዎች እንዲለቀቁ አዘው ምርመራውን ይመሩ በነበሩት ዳኛ ላይ ክስ አቅርበዋል።

ዋና አቃቤ ሕግ ግህሳን ኦዩይዲት በትናንትናው ዕለት የወሰዱት እርምጃ ለዓመታት ሳይንቀሳቀስ ለቆየው ምርመራ ሌላ ኪሳራ ተደርጎ ታይቷል።

ምርመራው ሀገሪቱን ታይቶ ከማይታወቅ የኢኮኖሚ ውድቀት ውስጥ ባስገባው እና በሙስና እና በብልሹ አስተዳደር በተተበተበው የሊባኖስን ገዥ ልሂቅ የመናድ አደጋ ሥጋት አሳድሯል።

የአቃቤ ሕጉ ውሳኔው የተሰማው ዳኛው ታሬክ ቢታር ከፍተኛ ውድመት ባደረሰው ፍንዳታ ላይ ተቋርጦ የነበረውን ምርመራ ዳግም ማንቀሳቀስ ከጀመሩ በኋላ ነው።

የክስ ሂደቱ የተንቀሳቀሰው ዋናው አቃቤ ህግ ጨምሮ በምርመራው የተከሰሱ ፖለቲከኞች ያነሷቸውን ሕግ ነክ ጥያቄዎች ተከትሎ ለአስራ ሦስት ወራት ተቋርጦ ከቆየ በኋላ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply