የቤተ አማራ የፋኖ ድምፅ ማህበር ድጋፍ አደረገ። ባህርዳር:- የካቲት 22/2014 አሻራ ሚዲያ የቤተ አማራ የፋኖ ድምፅ ማህበር እንደከዚህ ቀ…

የቤተ አማራ የፋኖ ድምፅ ማህበር ድጋፍ አደረገ። ባህርዳር:- የካቲት 22/2014 አሻራ ሚዲያ የቤተ አማራ የፋኖ ድምፅ ማህበር እንደከዚህ ቀደሙ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ብሎ ላመነባቸው ድጋፍ ሊያደርግላቸው ነው። የቤተ-አማራ የፋኖ ድምፅ ማህበር መቀመጫውን አዲስአበባ በማድረግ ከተለያዩ ሀገራትና አህጉራት በተሰባሰቡ ቅን አሳቢ የአማራ ተወላጆች የተመሰረተ ማህበር ነው። የማህበሩ ሰብሳቢ አቶ ፋንታሁን መንገሻ (ልጅ ቴዲ) ከዚህ ቀደም ከንሥር ብሮድካስት ጋር በነበረው ቆይታ “ቤተ-አማራ የፋኖ ድምፅ ማህበር የተመሰረተው በጦርነቱ ለተጎዱ የማህበረሰብ አካላት እና በህልውና ትግሉ የማይተካ መስዋዕትነትን ለከፈለው ፋኖ ድጋፍ ለማድረግ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም በጋሸና ጋይንትና መቄት ሲታገሉ ለነበሩ የፋኖ አባላት በትጥቅና ስንቅ የደገፉ ሲሆን ከሰሞኑ ደግሞ ከቅን ኢትዮጵያዊያን ገንዘብ በማሰባሰብ ለፍኖ ሞገስ ሞላ ማሳከሚያ የሚሆን 60,000 ብር ለፋኖ ደጀን ዋሴ እንዲሁ በትግል ወቅት የተጎዳ በመሆኑ 111,704 ብር ድጋፍ አድርገዋል። ከዚህ በተጨማሪም በፋኖ ዘመነ ካሴ ለሚመራ የፋኖ አደረጃጀት 200,000 እንዲሁም በፋኖ ምሬ ወዳጆ ለሚመራ የፋኖ አደረጃጀት ደግሞ 200,000 ብር ቤተ አማራ የፋኖ ድምፅ ማህበር ድጋፍ አድርጓል። የማህበሩ ሰብሳቢ ከንሥር ጋር በነበራቸው ቆይታ “ሰዎችን ለመርዳትና ለመረዳት የሚያስፈልገው ትላቅ ገንዘብ ሳይሆን የወገንን ህመም መረዳት የሚያስችል ትልቅ ልብ ነው” ብሏል። በተጨማሪም ስለ ማህበሩ መፃኢ እድል ሲያብራሩ “በአማራ ክልል እውቅና ያለው የሲቪክ ማህበር ሆኖ መቋቋምና በርካታ ማህበራዊ ፋይዳ ያላቸውን ተቋማት በመገንባት ማህበረሰቡን ለማገልገል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።” ትልቅ ህልም ሰንቀው ከሚያገኙት ቆርሰው ለወገኔ ለሚሉት በሰው ሀገር ተበታትነው በወገናቸው ፍቅር በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ አማራጮች ተሰባስበው ትልቅ ድጋፋቸውን ለሚያበረክቱት ውድ ኢትዮጵያዊያን በሰጣችሁት ላይ ይጨምርላችሁ ቅን ልቡናችሁን አይፍታባችሁ በማለት ዝግጅቴን እቋጫለሁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply