You are currently viewing #የቤተ ክህነቱ ትንሣኤ እየቀረበ ይመስላል። ምልክቶቹ  እየታዩ ነው። #በሊቀ ሊቃውንት  አባ ወልደ ትንሣኤ  አባተ! @ቅዱስ ሲኖዶስ ለብዙ ዘመናት  የህዝብን የካህናቱን የሊቃውንቱን ጥያቄ ወ…

#የቤተ ክህነቱ ትንሣኤ እየቀረበ ይመስላል። ምልክቶቹ እየታዩ ነው። #በሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ! @ቅዱስ ሲኖዶስ ለብዙ ዘመናት የህዝብን የካህናቱን የሊቃውንቱን ጥያቄ ወ…

#የቤተ ክህነቱ ትንሣኤ እየቀረበ ይመስላል። ምልክቶቹ እየታዩ ነው። #በሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ! @ቅዱስ ሲኖዶስ ለብዙ ዘመናት የህዝብን የካህናቱን የሊቃውንቱን ጥያቄ ወደ ጉን እየተወ በራሱ ምንገድ ብቻ እየተራመደ ውጤታማ ሳይሆን ቆይቶ ቤተ ክርስቲያንን ለውድቀት ዳርጎ ቆይቷል። ከወረዳ ቤተ ክህነት እስከ ሀገረ ስብከት ከጠቅላይ ቤተክህነት እስከ ቅዱስ ሲኖዶስ( ጽ)ቤት ድረስ በዘር በመንደር በብልሹ አሰራር በብልሹ አመራር ውስጥ ተዘፍቆ ሊቃውንቱ ሲሳደዱ ሊቃውንቱ ጦም ሲያድሩ ገዳማት ሲዘጉ መነኩሳት ሲበተኑ ህዝበ ክርስቲያኑ። በሃይማኖቱ ምክንያት ሲታረድ ሲሳደድ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ስትቃጠል የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች። በመንግስት ካድሪዎች ሲነጠቁ ሲኖዶሱ እና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመንግስት መጠቀሚያ ሁኖ ጠንካራ የሚባሉ ለሃይማኖቱ ይቆረቆራሉ የሚባሉ አባቶች ከዘመነ ደርግ እስከ ዘመነ ብልፅግና እየተገፉ እየተሳደዱ መከራ እየተቀበሉ ሲኖሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ልጆቹን ከመከራ ከቸግር ባለማዳኑ ቤተ ክርስቲያን ዘመን የማይተካቸውን ከፓትርያርክ እስከ ሊቃነ ጳጳሳት ከሊቃውንት እስከ ምዕመናኑ ድረስ ልጆቿን በአንባ ገነን መሪዎች እያጣች ቆይታለች። ወያኔ ለዘመናት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ጥሎት ያለፈው ጠባሳ ታሪክ በቅርብ ባያገምና ባይረሳም ብልፅግና በአራት አመት ውስጥ በቤተ ክርስቲያንና በህዝቦቿ ላይ የፈፀመው ግፍ ያደረሰው መከራ ዘመን የማይረሳው ነው። ቤተ ክርስቲያን ኢትዮጵያን ቆርበት እየፋቀች ቀለም እየበጠበጠች ታሪክና ድርሳንን ክብረ ነገስትና ፍታ ብሄርን ያረቀቀች ሀገር በጥላት እንዳት ወረር የዘመቻ ፅላት አሲዛ ሊቃንትን እየሰዋች ለሀገር እየገበረች ሀገርን ያቆየች የሀገር ባለውለታ ነበረች። ለምስክረም የሰማዕታተ ናግራን ደም ለመበቀል ወደ ደቡብ አረብ ከአፄ ካሌብ ጋር የዘመቱት የተድባበ ማርያም ፓትርያርክ ዘሙሴ ፔያሳ ላይ በጣልያን የተሰውት አቡነ ጴጥሮስ ጎሬ ኤልባቦር ላይ ለሀገር በጥላት እጅ የሞቱት አቡነ ሚካኤል ለምስክር ቢቆሙ ህይዎታቸውን በድቡሽት ላይ መስርተው ሀገር እያፈረሱ ሀገርን አሲዘው ተበድረው ፎቅ ለሚገነቡ ለከንቱ ሰዎችና ሀገር እንመራለን ባዮች በቅዱስ ሲኖዶስ ውስጥ የተደበቁ ቁማርተኞች አበው ለሀገር ያፈሰሱት ደም ባህር ሁኖ ያስጥማቸው ነበር። #የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕድ ቅዱስ ሲኖዶስ አሁን ከተደረገበት አዚምና ከገባበት ርግማን እየወጣ ይመስላል ይህም ለሃይማኖት ለሀገር ይቆረቆራሉ የሚባሉ አባቶችን ብፁዕ አቡነ አቡርሐምን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጅ አድርጎ መምረጡ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጽሐፊ አድርጎ መምረጡ የቤተ ክህነት ትንሣኤን ያመለክታል። እነዚህን ሁለቱንም አባቶች በቅርበት አውቃቸዋለሁ በተለይ ብፁዕ አቡነ አብርሐምን የሰውን ሐሳብ በፍጥነት የሚረዱ ከመናገር ይልቅ የሚያዳምጡ ከዘመነ ወያኔ እስከ መንደርተኛው ብልፅግና ድረስ እየታገሉ ያሉ መልካም እረኛ ትጉህ አባት ናቸው።ከፈጣሪ ዘንድ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ለቤተ ክርስቲያን የተሰጡ ገፀ በረከት ናቸው ብል ማገነን አይሆንም። ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስም በስደት ዓለም ውስጥ ሁነው ለህዝብ ዋጋ የከፈሉ አባትናቸው። ሁለቱም አባቶች በዘመኑ ደዌ እንዳለከፉ ሁነው በጥንቃቄ ከተራመዱ።ቤተ ክርስቲያንን እንደ ዓልአዛር ከተቀበረችበት መቃብር ውስጥ ያወጧትል የሚል ታላቅ እምነት አለኝ። ከላይ የዘመኑ ደዌ ብየ የጠቀስኩት ብፁዓን አባቶች መጠንቀቅ አለባቸው ብየ እንደ አንድ የቤተ ክርስቲያን ልጅ የምለግሳቸው ሃሳብ ቢኖረኝ የሀገር ሰው መስሎ ተቆርቋሪ ጠባቂ መስሎ ከሚመጣ ከሰፈር ከመንደር ሰዎች መጠበቅ አለባቸው እንድህ አይነት ሰዎች ከውሾች የከፉ ናቸው። ክርስቶስም ከውሾች ተጠበቁ ይላልና ውሻ ማለት ዘረኛ ሰው ነው። ብዙ ጠንካራ ሊቃነ ጳጳሳት አባቶችን ያጣናቸው በዚህ ምክንያት ስለሆነ ነው። ይህ ከሆነ ሁለቱም አባቶች ቤተ ክርስቲያን ከገባችበት ብልሹ አሰራር እንደሚያዎጧት ትልቅ እምነት አለኝ። አባቶቻችን ከገባችበት አዘቅትና መከራ ለማውጣት ለሚያደርጉት ትግል እኔም በስደት ዓለም ሁነው ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከሚታገሉ ወንድሞች ጋር በመሆን አባቶቻችን ከጎናቸው ሁኖ ለማገዝ አብሮ ለመቆም ቃል እየገባው አባቶቻችን መልካም የስራ ጊዜ እንድሆንላቸው ልባዊ ምኞቴ ከለሁበት ሀገር ሰሜን አሜሪካ ይድረሳቸው። በረከታችሁ ፀሎታችሁ አይለየኝ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ ሊቀ ሊቃውንት አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ አሻራ ሚዲያ ሰሜን አሜሪካ

Source: Link to the Post

Leave a Reply