የቤኒሻንጉል ክልል ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ገለልተኛ አማካሪ ቡድን ተመሠረተ

የቤኒሻንጉል ክልል ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ገለልተኛ አማካሪ ቡድን ተመሠረተ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ገለልተኛ አማካሪ ቡድን መመስረቱን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ፡፡
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ኮማደር አምሳሉ ኢራና እንደገለጹት÷ ወንጀልና የወንጀል ሥጋት በህብረተሰቡ ላይ የአካል፣ የህይወትና የንብረት ጉዳት ከማድረሱ ባሻገር የሚፈጥረው ስነ ልቦና ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡
ወንጀል የሚያስከትለውን የተወሳሰበ ችግር ለመፍታት የማኅበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ወሳኝ በመሆኑ ህብረተሰቡና ፖሊስ በጋራ በየአካባቢው የሚታየውን የወንጀል ሥጋት ለመቀነስና ተባብረው ለመሥራት ገለልተኛ አማካሪ ቡድኑ ቁልፍ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አቶ ሰይድ ባበክር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎትን ተግባራዊ ካደረገች ዓመታትን ያስቆጠረች ቢሆንም በክልሉ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ውጤታማ ሳይሆን መቆየቱን አንስተዋል፡፡
በክልል ደረጃ የተቋቋመው የገለልተኛ አማካሪ ቡድን አደረጃጀት በመፍጠር ሠላምን ለማስፈንና ወንጀልን ለመቀነስ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሠራ ሲሆን÷ በማኅበረሰቡ የቆዩ የግጭት አፈታት እሴቶችን በመጠበቅና በመጠቀም ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጎን ተሰልፎ የወንጀል መከላከል ሥራዎችን ለማከናውን ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ መናገራቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የቤኒሻንጉል ክልል ማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ገለልተኛ አማካሪ ቡድን ተመሠረተ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply