የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ኢ-መደበኛና ታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ባቀረብኩት ጥሪ እስካሁን እጅ የሰጠ ታጣቂ የለም አለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ህዳር…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ኢ-መደበኛና ታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ባቀረብኩት ጥሪ እስካሁን እጅ የሰጠ ታጣቂ የለም አለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ኢ-መደበኛና ታጣቂ ቡድኖች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ባቀረብኩት ጥሪ እስካሁን እጅ የሰጠ ታጣቂ የለም አለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከሰሞኑ የክልሉ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ‹43 የፀረ ሰላም ኃይሎች እጃቸውን ሰጥተዋል› በሚል ያቀረቡት መረጃ ትክክለኛ እንዳልሆነም የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ መለሰ በየነ ገልፀዋል፡፡ ምክትል ኮሚሽነሩ በተለይም ‹በመተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂ ቡድኖች እጃቸውን ሰጥተዋል› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ አካባቢውን ወደ ሰላም ለመመለስ የአገር መከላከያ ሰራዊት፣ የክልሉ ልዩ ኃይልና የፌደራል ፖሊስ በኮማንድ ፖስት ተቀናጅተው እየሰሩ ነው፤ ያሉት ኃላፊው ወደ ታላቁ ኅዳሴ ግድብ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለጊዜው በግልገል በለስ ከተማ እንዲቆሙ ተደርጓል ብለዋል፡፡ ስለምክንያቱ የጠየቃቸው ኃላፊው ጉባ ወረዳን ጨምሮ በመተከል ዞን በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የፀረ ሰላም ኃይሎችን ለመደምሰስ እርምጃ በመጀመሩ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ሆኖም ከእሁድ ኅዳር 27 ጀምሮ የቆሙት ተሽከርካሪዎች ወደ ግድቡ በመንቀሳቀስ መደበኛ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በመተከል ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የንፁሃን ግድያ፣ ማፈናቀልና ንብረት ማውደም በተደጋጋሚ የሚከሰት ጥቃት ሲሆን የክልሉ መንግሥትም አፋጣኝ እርምጃ እየወሰደ አይደለም በሚል ወቀሳዎች እየተነሱበት ይገኛል፡፡ አሐዱ ቴሌቪዥን

Source: Link to the Post

Leave a Reply