You are currently viewing የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ተሃድሶ በሚል በሬ እያረደ ሲቀልባቸው የነበሩ የጉሙዝ ታጣቂዎች ጭምር ወደ ጫካ በመግባት በንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ መሆኑን አመነ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ተሃድሶ በሚል በሬ እያረደ ሲቀልባቸው የነበሩ የጉሙዝ ታጣቂዎች ጭምር ወደ ጫካ በመግባት በንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ መሆኑን አመነ። አማራ ሚዲያ ማዕከ…

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ተሃድሶ በሚል በሬ እያረደ ሲቀልባቸው የነበሩ የጉሙዝ ታጣቂዎች ጭምር ወደ ጫካ በመግባት በንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀሙ መሆኑን አመነ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በርካታ አመራሮች ከታጣቂዎች ጋር እየተመሳጠሩ ነው በተለይ ደግሞ መንግስት በተደጋጋሚ በሚሰጣቸው መግለጫዎች መሬት ላይ ያለውን እውነታ እየደፈቀ ነው፤ ይህ ደግሞ በንፁሃን ደም መሳለቅ ነው በሚል ብዙ ተቃውሞዎች ሲነሱበት ቆይቷል። ጳጉሜ 4 ቀን 2013 በወቅታዊ ጉዳይ የሰጠው መግለጫ ግን እውነታውን የተቀበለ መሆኑን ያመለከተ ነው። ሙሉ መግለጫው እንደሚከተለው ቀርቧል:_ በመተከልና ካማሺ ዞኖች የሚንቀሳቀሰው የአሸባሪው የህወሃት ተላላኪ የሆነው ጸረ-ሠላም ኃይል “ሽፍትነትን” አንዱ የኑሮ አካል በማድረጉ በክልሉ በምንም ሁኔታ ሠላም እንዲኖር አለመፈለጉን በተግባር እያሳዬ ይገኛል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመሆን ባለፉት ጊዜያት በተለይም በሁለቱ ዞኖች የጁንታው የሕወሃት ቡድን ቀንደኛ ተላላኪ የሆነውን ጸረ-ሠላም ኃይል የፈጠረውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ከተወሰደው እርምጃ ባሻገር የተለያዩ አማራጮችን አስቀምጦ ሲሠራ ቆይቷል፡፡ የጥፋት ቡድኑ በተለያዩ አካባቢዎች በፈጠረው የጸጥታ ችግርና ጥቃት በሰው ሕይወት፣ በአካል፣ በንብረት ከደረሰው ጉዳት ባሻገር በርካታ ዜጎች ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው እንዲፈናቀሉ ምክንያት ሆኗል፡፡ የክልሉ መንግስት ችግሩን በሠላማዊ መንገድና በውይይት ለመፍታት ከፍተኛ የሆነ የበጀት፣ የጊዜ፣ የሰው ኃይል በመመደብ ለወራት የዘለቀ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል፡፡ በመተከልና ካማሺ ዞኖች ከሚንቀሳቀሰው የጥፋት ቡድኑ አባላት መካከል የተወሰኑት የቀረበውን “ሠላማዊ ድርድር” በመቀበላቸው የተሃድሶ ስልጠና እንዲወስዱም ተደርጓል፡፡ ነገር ግን መንግስት በሆደ ሰፊነት እና ንጹኃን ዜጎች አብረው እንዳይጎዱ በሚል ሠፊ ጊዜ ወስዶ ባለፉት ወራት ያስቀመጠውን የሠላማዊ ድርድር ዕድል እንደ ፍርሃትና ሽንፈት በመቁጠር የአሻባሪውን የሕወሃት ቡደን ተልዕኮ ለማስፈጸም የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱት የጥፋት ቡድኑ አባላት ሳይቀር ወደጫካ በመግባት አሁንም ድረስ በንጹኃን ዜጎች ላይ ጥቃት ከማድረስ ባሻገር ዜጎች ደክመው ያፈሩትን ሃብትና ንብረት መዝረፍን አጠናክረው ቀጥለውበታል፡፡ የክልሉ መንግስት የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በሚንቀሳቀሱ የጥፋት ቡድኖች ላይ የማያዳግም እርምጃ እንዲወስዱ ከዚህ ቀደም ለጸጥታ አካላት ትዕዛዝ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ የአሻባሪውን የሕወሃት ቡደን ተላላኪ ግን በክልሉ ዘላቂ ሠላም እንዳይኖር ለማድረግ አሁንም ድረስ ከሠላም ይልቅ “ሽፍትነትን” የኑሮው አንድ አካል አድርጎ በመቀጠሉ፣ ንጹኃን ዜጎችን ከመግደል፣ ንብረት ከመዝረፍና ህብረተሰቡ ተረጋግቶ እንዳይኖር ከማድረግ አልተቆጠበም፡፡ የክልሉ መንግስት እና የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት የችግሩን አሳሳቢነት በመረዳት ከሃገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከፌዴራል ፖሊስ፣ ከየክልሎች የልዩ ኃይል አባላት፣ ከሚሊሺያ አባላትና ከግል ታጣቂዎች ጋር በመሆን በጥፋት ቡድኑ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚወሰደውን እርምጃ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ ከወትሮ በተለዬ ሁኔታ ዝግጅት አድርጓል፡፡ በተለይም በመተከልና ካማሺ ዞኖች ጸረ-ሠላም ኃይሉ በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ይህንን አውቀው ራሳቸውን ከጥፋት ቡድኑ እንዲነጥሉ የክልሉ መንግስት በጥብቅ ያሳስባል፡፡ በተጨማሪም መንግስት ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለሚወስደው እርምጃ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች፣ የመንግስትና የግል ታጣቂዎች፣ ወጣቶች፣ እንዲሁም ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ለህግ ማስከበር እርምጃው ቅድሚያ በመስጠት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ የክልሉ መንግስት እና የመተከል ዞን የተቀናጀ ኮማንድ ፖስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply