የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ሙሉ በሙሉ በጭለማ እንዲዋጥ ያደረገ ስርቆት መፈፀሙ ተነገረ።

ከመንዲ አሶሳ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመ ስርቆት ምክንያት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሙሉ በሙሉ የኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ጋይል አሳውቋል።

በክልሉ ” መንደር 48 ” በተለምዶ አንበሳ ጫካ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ ምሰሶ አካላት ላይ በተፈፀመ ስርቆት መስመሩን የሚሸከሙ ሁለት የብረት ምሰሶዎች ወይም ታወሮች ወድቀዋል፡፡

በዚሁ የተነሳ ከመስመሩ ኃይል ሲያገኙ የነበሩት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መዲና አሶሳ ከተማ እና የአሶሳ ዞን ወረዳዎች በሙሉ የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል።

ከዚህ በፊትም በክልሉ ባምባሲ በተባለ አካባቢ በሥርቆት የተነሳ ኃይል ተቋርጦ የነበረ ሲሆን አሁን ለኃይል መቋረጥ ምክንያት የሆነው አካባቢ ከአሶሳ ከተማ ወደ 30 ያህል ኪሎ ሜትሮች ርቀት እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡

የወደቁ የኤሌክትሪክ ምሰሶዎችን በጊዜያዊነት በእንጨት ምሰሶዎች ለመተካት ጥረቶች የተጀመሩ ሲሆን ጥገናውን አጠናቆ ለአካባቢዎቹ ኃይል ለመስጠት እስከ ሦስት ቀን ድረስ ሊወስድ ይችላል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፤ የኤሌክትሪክ መሰረተልማቶችን መጠበቅ በየደረጃው ያሉ የሁሉም መስተዳድር አካላት ኃላፊነት መሆኑን አስገንዝቦ የመስተዳድር አካላቱ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪ አድርጓል።

ጥገናው ተጠናቆ ወደአገልግሎት እስኪመለስ ድረስ ህብረተሰቡ በትዕግስት እንዲጠብቀም ጠይቋል።

በአባቱ መረቀ

ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply