የቤንሻንጉል ክልል መንግስት ያወጣው መግለጫ አንድምታው ሲገለጽ  ራስን በራስ የማስተዳደር መብቴ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ይፈቅድልኛል ማለት እንደሆነ ተገለጸ፡፡…

የቤንሻንጉል ክልል መንግስት ያወጣው መግለጫ አንድምታው ሲገለጽ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቴ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ይፈቅድልኛል ማለት እንደሆነ ተገለጸ፡፡…

የቤንሻንጉል ክልል መንግስት ያወጣው መግለጫ አንድምታው ሲገለጽ ራስን በራስ የማስተዳደር መብቴ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ይፈቅድልኛል ማለት እንደሆነ ተገለጸ፡፡ አሻራ ሚዲያ ታህሳስ፡-07/04/13/ዓ.ም ባህር ዳር የቀይ ሰው ደም መጠጣት፣ ጉበትና ኩላሊት መብላት ከበሽታ እንደሚያድን በሚያምን ማህበረሰብ ዘንድ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት የዘር ፍጅት መፈፀሚያ ህጋዊ ፈቃድ ተደርጎ ቢወሰድ የሚገርም አይደለም። በክልሉ የሚስተዋለውን ጎጅ ባህል ከማስቀረት ይልቅ አስከፊውን የአውሬዎች ግብር በፖለቲካ አዋዝቶ ስልጣን ላይ ማውጣት የህዝብን በደል ማክፋት እንጂ ዲሞክራሲ አይደለም። የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስት የአማራ ህዝብ ለረጅም ጊዜ ሲታረድና ሲጨፈጨፍ ማስቆም እንዳልቻለ ተረጋግጧል። ከመንግስትም ከህዝብም በኩል የክልሉ መንግስት ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ሲጠየቅ ቆይቷል። የክልሉ መንግስት ግን በክልሉ የሚፈፀመውን የሰው ልጆች መታረድ ከማስቆም እና ወንጀለኞች ላይ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ሃላፊነቱን እንዲወጣ የቀረበለትን ጥያቄ የራስን በራስ የማስተዳደር መብትን መጋፋት አድርጎ ወስዶታል። ከምንም በላይ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ፀረ ህዝብ ሃይሎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚነሳው ጥያቄ የክልሉን መንግስት ልብ ፍርሃት ለቆበታል። አንድ የክልል መንግስት ለህዝብ ደህንነት የሚጨነቅ ከሆነ በወንጀለኞች ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ይደግፋል እንጂ በክልሉ ላይ ጦርነት እንደተከፈተ አድርጎ መውሰድ አልነበረበትም። ዳሩ ግን የክልሉ መንግስት የተሰጠውን ክልል የማስተዳደር ሃላፊነቱን ባግባቡ እንዲወጣ፣ ሁኔታው ከቁጥጥሩ በላይ ከሆነም ከሌሎች ክልሎች እገዛ እንዲጠይቅ፣ አቅሙ አለኝ ካለም በክልሉ የሚፈፀመውን የዘር ፍጅት ባስቸኳይ እንዲያስቆም የተጠየቀውን ጥያቄ ገዳዮቼን አትንኩብኝ ብሎ ዘግቶታል። የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ባወጣው መግለጫ ለአቅመ ራስን በራስ ማስተዳደር ሃላፊነት እንዳልበቃ እና በመተከል የሚፈፀመው አረመኔያዊ ተግባር ከክልሉ መንግስት ፖለቲካዊ እሳቤ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው አረጋግጧል። የክልሉ መንግስት በግልፅ ክልሌ የፈለኩትን የዘር ፍጅት ብፈፅም ራስን በራስ የማስተዳደር መብቴ ይፈቅድልኛል ማንም ሊናገረኝ አይገባም ብሎ መግለጫ አውጥቷል። ይህ በክልሉ የሚፈጠረው ቀውስ በክልሉ መንግስት እንደሚደገፍ እና ለወንጀለኞችም ከለላ በመሆን የአማራ ህዝብ የዘር ፍጅት ውስጥ እጁ እንዳለበት የሚያረጋግጥ ነው። በክልል አስተዳደር ደረጃ ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በክልሉ ያለውን የሌላ ብሄር ዘር ማጥፋት መስሎ የሚታየው አመራር መኖሩ በሀገራችን ላለው ፖለቲካ ሀፍረት ነው ብልፅግና ለተሰኘው ፓርቲ ደግሞ ቅሌት ነው። በመሆኑም ራስን በራስ የማስተዳደር መብት በክልሉ ያለውን ህዝብ ደህንነት ከመጠበቅ ጋር የሚሰጥ ሃላፊነት እንጂ ህዝብን በማንነቱ ምክንያት ለመጨፍጨፍ ፈቃድ የሚሰጥ ባለመሆኑ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አስተዳደር የፌደራል መንግስቱ አስቸኳይ ማስተካከያ ሊያደርግበት ይገባል። ከዚህ በተጨማሪም የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ ላይ ያሉ አረመኔ ሃይሎችን የክልሉ መንግስት ለማስቆም ፈቃደኛ ባለመሆኑ እና የአማራ ህዝብም የሚደረገውን ጭፍጨፋ ባስቸኳይ እንዲቆም እየጠየቀ በመሆኑ የፌደራል መንግስቱ ባስቸኳይ እንዲያስቆም አለያም የአማራ ክልል መንግስት ህዝቡን ከጨፍጫፊዎች መታደግ እንዳለበት ምንጮች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ይህን ሳይሆን ቀርቶ ግን የአማራ ህዝብ ራስን በራስ በማስተዳደር መብት ሽፋን የዘር ፍጅት ሲፈፀምበት በዝምታ የማናይ በመሆኑና ማንኛውም ህዝብ ራሱን ከጥቃት የመከላከል የተፈጥሮ መብት ያለው በመሆኑ ህዝብ የራሱን አማራጭ ለመውሰድ እንደሚገደድ መታወቅ ይኖርበታል። ስለዚህ ለወንጀለኛ ቡድን መደበቂያ የሆነውን የቤንሻንጉል ክልል መንግስትን የፌደራል መንግስት ተጠያቂ ማድረግ ግዴታው መሆኑን ማወቅ አለበት፡፡ ዘጋቢ፡- ጥላሁን ታምሩ

Source: Link to the Post

Leave a Reply