የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመድሀኒት እና በህክምና ግብዓቶች ዕጥረት መቸገሩ ተነገረየቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የመድሃኒት እና የህክምና ግብዓቶች ዕጥረት ችግር እንደሆነበት ገልጿል፡፡በ…

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በመድሀኒት እና በህክምና ግብዓቶች ዕጥረት መቸገሩ ተነገረ

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጤና ቢሮ የመድሃኒት እና የህክምና ግብዓቶች ዕጥረት ችግር እንደሆነበት ገልጿል፡፡

በክልሉ ያለዉ የጸጥታ ችግር እንዲሁም እንደ አገር ያለዉ የህክምና ግብዓቶች ዕጥረት እንደምክንያት እንደሚነሳ በክልሉ ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ አብዱልሙኔም አልበሽር ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በጸጥታ ሁኔታዉ ምክንያት የህክምና ግብዓቶች በአየር ወደ ክልሉ እንዲገቡ እንዲሁም በእጀባ ጭምር እንዲገባ ያደረግን ቢሆንም በቂ አይደለም ያሉት አቶ አብዱልሙኔም፤ የህብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላት የሚችል አይደለም ነዉ ያሉት፡፡

ከአዲስ አበባ ወደ ክልሉ መዲና አሶሳ ያለዉ መንገድ ከተዘጋ ከ4 ዓመት በላይ ሆኖታል ያሉት ምክትል ሃላፊዉ ፤ በዚህ ምክንያት በአየር ትራንስፖርት መድሃኒቶችን ለማስገባት ቢሞከርም ግን በቂ አይደለም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የጤና ስርዓቱን ወደነበረበት ለመመለስ በክልሉ መንግስት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ቢኖሩም በቂ አይደሉም ያሉት አቶ አብዱልሙኔም፤ በተጨማሪ ከበጀት ጋር ተያይዞ ያለዉ ጉዳይም አስቸጋሪ ሆኖ ቀጥሏል ነዉ ያሉት፡፡

የተፈጠረዉን የግብዓት እና የመድሀኒቶች ዕጥረት ችግር ለመፍታት ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር በጋራ እየሰሩ መሆናቸዉንም ነዉ የገለጹት፡፡

እስከዳር ግርማ

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply