የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ስራ መግባት ያልቻሉ በርካታ የህክምና ተቋማት መኖራቸዉን ገለጸ፡፡በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የወደሙ እና ዛሬም ወደ ስራ ያልገቡ በርካታ…

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወደ ስራ መግባት ያልቻሉ በርካታ የህክምና ተቋማት መኖራቸዉን ገለጸ፡፡

በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተከሰቱ ግጭቶች ምክንያት የወደሙ እና ዛሬም ወደ ስራ ያልገቡ በርካታ የጤና ተቋማት መኖራቸዉን ሰምተናል፡፡

ግጭቱ ተስፋፍቶ በነበረባቸዉ የካማሺ እና መተከል ዞን እንዲሁም ማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳ ያሉ የህክምና ተቋማትን አድሰን ወደ ስራ ማስገባት ብንችልም አሁንም በርካቶቹ ግን ወደ ስራ አልገቡም ሲል የክልሉ ጤና ቢሮ ለጣቢያችን አስታዉቋል፡፡

በክልሉ ጤና ቢሮ የፕሮግራም ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ አብዱልሙኔም አልበሽር በክልሉ መንግስት የተደረጉ ድጋፎች ቢኖሩም ግን በቂ ባለመሆናቸዉ ብዙዎቹ ወደ ስራ እንዳይገቡ አድርጓቸዋል ብለዋል፡፡

በክልሉ ወደ 26 ወረዳዎች ቢኖሩም በልዩ ሁኔታ የተመረጡ 5 ወረዳዎች ላይ በመልሶ ማቋቋም ፕሮጀክት ስራዎች ተሰርተዉ አንዳንዶቹን ተቋማት ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየሰራን ነዉ ሲሉ ምክትል ሃላፊዉ ተናግረዋል፡፡

ነገርግን አሁንም ስጋቱ ሰፊ ነዉ የሚሉት አቶ አብዱልሙኔም፤ አሁንም ድረስ ከክልሉ አቅም በላይ የሆኑ እና እድሳት ተደርጎላቸዉ ወደ ስራ መግባት ያልቻሉ በርካታ የጤና ተቋማት መኖራቸዉ ሊታወቅ ይገባል ብለዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply