You are currently viewing የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የልዩ ኃይል አዛዥን ጨምሮ ሌሎች ከበታች አመራሮች መካከልም ለጉምዝ ሽፍታ ቡድን መረጃ አሳልፎ በመስጠትና በሌላም ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የልዩ ኃይል አዛዥን ጨምሮ ሌሎች ከበታች አመራሮች መካከልም ለጉምዝ ሽፍታ ቡድን መረጃ አሳልፎ በመስጠትና በሌላም ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል…

የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የልዩ ኃይል አዛዥን ጨምሮ ሌሎች ከበታች አመራሮች መካከልም ለጉምዝ ሽፍታ ቡድን መረጃ አሳልፎ በመስጠትና በሌላም ትብብር በቁጥጥር ስር ውለዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በርካታ አመራሮች በተለያዩ ጊዜያት ከጉምዝ ሽፍታ ቡድን ጋር እየተባበሩ ነው፣ ንጹሃንን ከእልቂት አልታደጉምና ሌሎች ምክንያቶችን በመጥቀስ እየታሰሩ ነው ሲባል ብዙም ሳይቆዩ የተፈተዋል ዜናን መስማት የተለመደ እየሆነ ነው። የተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም መንግስት መዋቅሩን ለመፈተሽ ባለመቻሉ ንጹሃን ማንነታቸው እየተቆጠሩ ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጋር በሚተባበረው የጉምዝ ሽፍታ ቡድን እየተገደሉ፣ እየተጠቁ፣ እየተፈናቀሉና እየተዘረፉ ነው በሚል ሲወቅሱ ሰንብተዋል። መንግስት ምንም ቆርጦ የገባ ባይሆንም ከሰሞኑ በሶስት አመራሮች ላይ እርምጃ መውሰዱ ውስጡን ቢፈትሽ ሽፍታው ጫካ ብቻ ሳይሆን መሀል ከተማ ለዛውም በመዋቅሩ ውስጥ እንደሆነ ይረዳዋል ይላሉ አሚማ ያነጋገራቸው ምንጮች። አሁንም በአስቸኳይ ከላይ እስከታች መዋቅሩን በመፈተሽ ንጹሃንን ከተደራጀ ጥቃት እንዲታደግ ተጠይቋል። ከሰሞኑ በቁጥጥር ስር የዋሉትም:_ 1) ኮማንደር ኤዶሳ ጎሹ፣ 2) አቶ ገበየሁ ጀጎዴ፣ 3) አቶ መልካሙ በሹዋለ የቤጉ የልዩ ኃይል አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ኢዶሳ ጎሹ ህዳር 2 ቀን 2014 መረጃ ለሽፍታ ቡድኑ ሲያቀብሉ በኮማንድ ፖስቱ ስለመያዛቸውና በአሶሳ ማ/ቤት ታስረው እንደሚገኙ ለአሚማ የደረሰው መረጃ አመልክቷል። በተመሳሳይ ጥቅምት 30 ቀን 2014 አቶ ገበየሁ ጀጎዴ የተባሉ የመተከል ዞን ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ በቁጥጥር ስር ውለዋል። አቶ ገበየሁ የድባጤ አካባቢ ተወላጅና በአካባቢው ከተከሰተው ጥቃት ጋር እጃቸው ሊኖርበት እንደሚችል ነው የመረጃ ምንጮች የጠቆሙት። ከጉምዝ ሽፍታ ወርቅ በመቀበል ሽጠው ጥይት በመግዛት ለቡድኑ ለማስረከብ እየሰሩ ሳለ ከእነ ገንዘቡ እጅ ከፈንጅ ተይዘው ነው በግልገል በለስ ማ/ቤት በእስር ላይ የሚገኙት ተብሏል። ከሳምንት በፊት የመተከል ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መልካሙ በሹዋለ ደግሞ ለሽፍታ መረጃ ሲያቀብሉ ተገኝተዋል በሚል ተይዘው በግልገል በለስ ማ/ቤት ይገኛሉ። ከመተከል ኮማንድ ፖስት ሻምበል ተሾመን ደውለን ለማነጋገር ብንሞክርም መረጃ ለመስጠት ስልጣኑ የለኝም በማለት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የቤጉ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሌ ሀሰንና ም/ፕሬዝዳንት አቶ ጌታሁን በጉዳዩ ዙሪያ አሁን አይመቸንም በማለት መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። ተጨማሪ መረጃ እንዳገኘን የምንመለስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply