የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በ2014 በጀት ዓመት የዕቅዱን 85 በመቶ በማሳካት ከአንድ ቢሊዮን 40 ሚሊዮን ብር…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/RsMcW6BrDoeH9iksNWSTy43xtqjzEHvIyMdtUyDei-TXt3Is0KqXCgMYiw8iGW_rS6DIKfn6UnUCsf_LXhKYOVLiv1_htsiBAG8Cr8htbCnaibOp2dmUJvEyRm6uFkz9atE-qU56IuPNx8W6kFxXTpP7PWRHL93fkKbs3_OcWAIdF4oJwja_COHB8yoULtrAqQsAjXNns-oRtMZdhCtxuObueSiG1Ld7rG53iz7sp5F7UvvZOhBQn642Yak5PElphQ8g3LL9KUGIxCRgN9-2b2EmkJIUJ0cMVmMIva23BWuwsvvB0Nh6VZATukkvuz7K-rLCcLNA7D4rsYYSQ1rHzQ.jpg

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር በ2014 በጀት ዓመት የዕቅዱን 85 በመቶ በማሳካት ከአንድ ቢሊዮን 40 ሚሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ገቢ ማግኘቱን የአስተዳደሩ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ቴዎድሮስ ንዋይ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል፡፡

በ2014 በጀት ዓመት 12 የሎተሪ አይነቶችን ወደ ገበያ ይዞ መግባቱን ያነሱት አቶ ቴዎድሮስ፣ በዚህም የተጣራ 278.6 ሚሊዮን ብር ትርፍ ሲያገኝ ይህም ከዕቅዱ 73.7 ሚሊዮን ብር ከፍ ያለ መሆኑንም ነዉ የተናገሩት፡፡

የህዝብ ግንኙነት ሀላፊዉ እንዳሉት፣ ቢንጎ እና ፈጣን እንዲሁም የገና ፣ እንቁጣጣሽ ፣ ዝሆን እና ትንሳዔ ሎተሪዎች በብዛት የተቆረጡ ሎተሪዎች ናቸዉ፡፡

በቅርቡ በአጭር የጽሁፍ መልዕክት ከኢትዮ ቴሎኮም ጋር በመተባበር ስራ የጀመረዉ የአድማስ ሎተሪ ተደራሽነት ከፍተኛ መሆኑንም ያነሱት አቶ ቴዎድሮስ፣ ማንኛዉም ሰዉ በቤቱ ሆኖ መቁረጥ እና መጫወት በመቻሉ ሁሉም ጋር መድረስ ተችሏል ነዉ ያሉት፡፡

በተጨማሪም ከቤቲንግ እና በፍቃድ ከሚሸጡ ሎተሪዎች በአጠቃላይ 199.1 ሚሊዮን ብር ትርፍ መገኘቱንም ነግረዉናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በአጠቃላይ 52 የስፖርት ዉርርድ ቤቶች ከብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ጋር በጋራ እየሰሩ እንደሚገኙም አቶ ቴዎድሮስ ገልጸዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ
ሐምሌ 04 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply