የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ  ያዘጋጀው እና የሀገሪቱን ሁኔታ የገመገመት ሰነድ  ከኢህአዴግ  ዘመኑ እንደማይለይ  የብልጽግና  አመራሮች እየተናገሩ ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013) የብል…

የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ያዘጋጀው እና የሀገሪቱን ሁኔታ የገመገመት ሰነድ ከኢህአዴግ ዘመኑ እንደማይለይ የብልጽግና አመራሮች እየተናገሩ ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013) የብል…

የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ያዘጋጀው እና የሀገሪቱን ሁኔታ የገመገመት ሰነድ ከኢህአዴግ ዘመኑ እንደማይለይ የብልጽግና አመራሮች እየተናገሩ ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 23፣ 2013) የብልፅግና ሰነድ እንደ ኢህአዴግ ዘመኑ ሁሉ አማራን በብሄረሰቦች ጠላትነት የሚፈርጅ ሲሆን፣ የህገመንግስት ጥያቄንም በአሃዳዊነት እና በዘውዳዊነት መስሎ ያቀረበ ነው፡፡ በመድረኩ አንዳንድ የአማራ ብልፅግና አመራር በዚህ ሁኔታ ከብልፅግና ጋር አንቀጥልም የሚል አስተያዮት የሰጡ ሲሆን፣ አብይ አህመድ መውጣት ትችላለችሁ የሚል አስተያየት ሰጥተኃል፡፡… በኃላ ግን ውስን የአማራ ብልፅግና አመራሮችን በግል ሰብሰብው በጉዳዮ ዙሪያ እንደተወያዮ የአሻራ ምንጮች ተናግረዋል፡፡ እንደ አሻራ የመረጃ ምንጮች ብልፅግና ራሱን ከኢህአዴግ የሚለይበት አንዳችም መስመር አልሰራም፡፡ ውህደቱም መቀላቀል ነው ወይስ የተፋላሚዎች ግንባር ነው እየተባለ ነው፡፡ ራሳቸው ብልፅግናዎች ብልፅግና በመመስረቱ ጠብ የሚል ሀገራዊ ጥቅም እንዳልተገኘ እየተናገሩ ነው፡፡ የመንግስታዊነት ባህሪ የራቀው የዶክተር አብይ አመራርም የሚይዘው እና የሚጨብጠው አጥቶ ብልፅግና የማዕበል ዋናተኛ ድርጅት ሆኗል፡፡ በብልፅግ አለመቻል ውስጥ ዜጎች በገፍ እየተፈናቀሉ እና እየሞቱ ነው፡፡ መተከል ዛሬም የአማራዎች ቄራ ሆኗል፡፡ መተከል አልተረጋጋም፡፡ ብልፅግና መፍትሄ ለማመንጨትም ሆነ ለመስራት ተስኖታል፡፡ የውጭ መንግስታትም ብልፅግናን ተጨማሪ የፖለቲካ ድርድር እና ውይይት ያስፈልጋል እያሉት ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply