የብሔራዊ መታወቂያ ወንጀልን ለመከላከል ይረዳል ተባለ።

የብሔራዊ መታወቂያ የራሱ መለያ ቁጥር እንዲኖረው በመድረጉ የማጭበርበር ወንጀልን ለመከላከል ይረዳል ተብሏል።

መንጃ ፍቃድ እና የቀበሌ መታወቂያ የመሳሰሉ ሰነዶች ሀሰተኛ ሆነው የሚቀርብበት መንገድ መኖሩን ያነሱት የብሔራዊ መታወቂያ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አቤኔዘር ፈለቀ የብሔራዊ መታወቂያ የግለሰቦች ትክክለኛ ማንነትን ማረጋገጥ የሚያስችል ነው ሲሉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ሆኖም የብሔራዊ መታወቂያ የቀበሌ መታወቂያንም ሆነ ሌሎች ሰነዶችን የሚተካ ሳይሆን ተመጋጋቢ ሆኖ የቀረበ መሆኑ አፅንኦት ሊሰጠው ይገባል ብለዋል።

አቶ አቤኔዘር በተለያዩ ቦታዎች የብሔራዊ መታወቂያ እናትማለን የሚሉ አካላትን ህጋዊነታቸው የተረጋገጠ ነው ወይንም አይደለም የሚለው ላይ ለመወሰን በሂደት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

መስሪያ ቤቱ አሁን ላይ የግብአት እጥረቶች እንዳሉበትም አንስተዋል።

ችግሩን ለመቅረፍም ከአለም ባንክ 3 መቶ 50 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኘት እንደቻሉ እና ከዚህም ውስጥ 50 ሚሊዮን ዶላሩ ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች እና ለተፈናቃዮች የሚውል ሲሆን 300 ሚሊየኑ ደግሞ ለተለያዮ ስራዎች እንደሚውል ተናግረዋል።

እስከ አሁን ወደ 4 ሚሊዮን የሚጠጉ የማህበረሰባችን ክፍሎች የብሄራዊ መታወቂያን ለማግኘት እንደተመዘገቡ አቶ አቤኔዘር ተናግረዋል።

በሐመረ ፍሬው
መጋት 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply