የብሔራዊ ስፖርት ም/ቤት ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

የብሔራዊ ስፖርት ም/ቤት ስብሰባ መካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ስብሰባ በስካይ ላይት ሆቴል መካሄድ ጀምሯል ።
በስብሰባው የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እና የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ሂሩት ካሳው ፣የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ፣ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት ተገኝተዋል ።
በስብሰባው የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት የስብሰባ ስነ ስርዓት ደንብ እና በተሻሻለው የሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራት ማቋቋሚያ መመሪያ ላይ በመወያየት የሚፀድቅ መሆኑን ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የብሔራዊ ስፖርት ም/ቤት ስብሰባ መካሄድ ጀመረ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply