የብሪታንያው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር ከአመታት ትርምስ በኋላ ብሪታኒያን እንደገና ለመገንባት ቃል ገብተዋል፡፡ አዲሱ የቢሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ኬር ስታርመር ከአመታት ግርግር እና…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/PhEsleVwdO7l_OBxrXd1jGtySFIJJvNoJeGG2DFX0GrEjTVOB6WcwWy5p7B7FaamAns9yq6KVRpkW0wLyLgfmZDEMuZvJ1_Kjd3py35Pzid0e4qea65azW2dtmVDNV4DW5E2ZUNNWWRSZfE0H4TsYK_ex7OY5CIbLmjoq9GtwP2gc50Jjju2NPiPM987_kBms1kMm8hpkC-aXG-8eXWbvmspi-rukGPXKN3MpuuiLtrWeAJLZ8qTn06VaNU5Dyw06I5xAXWObFS-StmpP8CzxGrEykTmcxbM1d3_uxXUhLbKFClwdkAX2yvjxkMfZdg4Dkxaw4Dod-0e1mgdd6E7pQ.jpg

የብሪታንያው አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር ከአመታት ትርምስ በኋላ ብሪታኒያን እንደገና ለመገንባት ቃል ገብተዋል፡፡

አዲሱ የቢሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ኬር ስታርመር ከአመታት ግርግር እና ውዝግብ በኋላ ፖለቲካ ውስጥ ያለውን ትኩሳት ማስወገድ እንደሚፈልጉ በመግለፅ ከፍተኛውን የምርጫ አብላጫቸውን ተጠቅመው ሀገሪቱን መልሶ ለመገንባት በትላንትናው እለት ቃል ገብተዋል፡፡

የሌበር ፓርቲ መሪ ሰር ኪር ስታርመር የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ምርጫን በማሸነፍ ቀጣዩ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ ማንኛውም ለውጥ ግዜ እንደሚወስድ አንስተው በመጀመሪያ ግን በፖለቲካ ላይ እምነትን ማደስ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

“ይህ የመተማመን እጦት የሚፈወሰው በቃላት ሳይሆን በተግባር ብቻ ነው ይህንን አውቃለው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

የተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሪሺ ሱናክ የወግ አጥባቂው (ኮንሰርቫቲቭ) ፓርቲ ከአጠቃላይ 650 ወንበር በታሪኩ አነስተኛ የሆነ 121 ወንበር ብቻ አግኝቶ ምርጫውን ሲሸነፍ የሌበር ፓርቲ በበኩሉ 412 የምክር ቤቱ ወንበሮችን በማግኘት በከፍተኛ አብላጫ ምርጫውን ማሸነፉ ይታወሳል፡፡

በሐመረ ፍሬው
ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply