የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ዳግም የእንቅስቃሴ እቀባ ማድረግ ከእብደት ይቆጠራል አሉ::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20፣ 2013 የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ዳግም የእንቅስቃሴ እቀባ ማድረግ ከእብደት ይቆጠራል አሉ:: የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ አቅልለው በማየታአቸው በርካታ ብራዚላዊያንን ዋጋ አስከፍለዋል:: ተብለው የሚተቹት ፕሬዚዳንቱ የእንቅስቃሴ ገደቦችን አጥብቀው እየተቃወሙ ነው፡፡

አብዛኞቹን የአውሮፓ ሀገራትን ጨምሮ በመላው ዓለም ወረርሽኙ ዳግም እየተስደፋፋ መሆኑን ተከትሎ አዳዲስ መመሪያዎች እያወጡ ሲሆን ቦልሶናሮ ግን እምጃውን ርባና ቢስ በማለት ተችተውታል፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው ክትባትን አስመልክተው በሰጡት መግለጫም ለማይጠቅም ነገር
ገንዘብ አናባክንም የሚል አስተያየት ነው የሰጡት፡፡

የሳኦፖሎን አስተዳዳሪ በስም ጠቅሰው ባስተላለፉት መልዕክትም ቻይና ለጀመረችው ምርምር ገንዘብ አውጥተን የክትባት መድሀኒቱን አንገዛም ብለዋል፡፡
ገንዘቡ የእኔ ሳይሆን የህዝቡ ነው ያሉት ቦልሶናሮ በህዝብ ገንዘብ እኔ አላዝም እናም ክትባቱን እንዳታስቡት በማለት አቋቸውን አሳውቀዋል፡፡
እሳቸውየ በሽታውን ክብደት አሳንሰው ቢመለከቱትም የ159 ሺህ ብራዚካዊያነውን ህይዎት መቅጠፉ ይታወቃል፡፡ ብራዚል በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ብዙ ሰዎች ከተያዙባቸው ሀገራት መካከል በሶስተኛ በሟቾች ብዛት ደግሞ ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply