የብራዚል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ፣እየደረሰባቸው ያለውን የመፈንቅለ መንግስት ውንጀላውን አስተባብለዋል።የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ ከአንድ አመት በፊት ስልጣናቸውን ከ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/DKJyEUEAyEnfS6gM0en6h12LElkLxljdxPdjuK0w9LP1NPzQ0whfdu8v0rISF6Cdn_mTWTAkPtbqgQoJaib5CM4licCI7Jp2rx3tCbHxzvRZ_5vMdzn3U-xNmXAhW4DbezBPa3-VNJLpPK_mIiTX2CqSZgSONx8qmLP34JcsQpl_RQZoCv7Dg7Gbdo5dkoJl8R1BMDRL6Nxkp2VUiFI1CtHuVwlkEJ5pO95VIbzGzHjq34LdothHMqNq-3Mw4pGeyOUv8SuaF5ShCqcPJ1SVgcWz1kg9o3NiksW-ZXD-MpIhpNGOeR15vuoRr63URF_o_B69cVO8X8JUHsAOhZAppw.jpg

የብራዚል የቀድሞ ፕሬዝዳንት ቦልሶናሮ፣እየደረሰባቸው ያለውን የመፈንቅለ መንግስት ውንጀላውን አስተባብለዋል።

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ጃየር ቦልሶናሮ ከአንድ አመት በፊት ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ የሃገሪቱ የፖለቲካ ስርዓት እንዳይረጋጋ ሲያሴሩ ነበር የሚል ክስ ይቀርብባቸውል፡፡

በሳኦ ፓውሎ ውስጥ በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቸ እንደተናገሩት የሚደርስባቸው መፈንቅለ መንግስት ክስ “ሃሰት” ነው ብለዋል።

በሕዝብ ህንፃዎች ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ተብለው ለተፈረደባቸው በመቶዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው ይቅርታ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።

በ2022 ምርጫ ከተሸነፉ በኋላ ቦልሶናሮ ያልተሳካለት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ እንዲደረግ አነሳስተዋል በሚል ቀደም ሲል ፖሊስ ምርመራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

የ68 አመቱ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያለፈውን በመርሳት ብራዚል ወደ ፊት በተሸለ መልኩ እንድትቀጥል ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

በ2026 ስለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫም ዋና ተፎካካሪ እንደሚሆኑ ከወዲሁ ፍንጭ መስጠታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply