You are currently viewing የብአዴን አመራሮች የሸዋሮቢት እና አካባቢው ሚሊሾችን በመሰብሰብ በፋኖዎች ላይ አቅደውት የነበረው ሴራ መክሸፉ ተገለጸ፤ “ኦነግ ሸኔ በራችን ድረስ መጥቶ እየገደለን እንዴት ሃገር ጠባቂ የሆነ…

የብአዴን አመራሮች የሸዋሮቢት እና አካባቢው ሚሊሾችን በመሰብሰብ በፋኖዎች ላይ አቅደውት የነበረው ሴራ መክሸፉ ተገለጸ፤ “ኦነግ ሸኔ በራችን ድረስ መጥቶ እየገደለን እንዴት ሃገር ጠባቂ የሆነ…

የብአዴን አመራሮች የሸዋሮቢት እና አካባቢው ሚሊሾችን በመሰብሰብ በፋኖዎች ላይ አቅደውት የነበረው ሴራ መክሸፉ ተገለጸ፤ “ኦነግ ሸኔ በራችን ድረስ መጥቶ እየገደለን እንዴት ሃገር ጠባቂ የሆነውን ፋኖ እናሳድዳለን?” በሚል አጥብቀው መቃወማቸው ነው የተሰማው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ/ም … አዲስ አበባ ሸዋ በሽዋሮቢት ታህሳስ 6 ቀን 2015 ዓ/ም ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት ምክንያት በማድረግ ከዞን እስከ ወረዳ ያሉ የብአዴን አመራሮች የሽዋሮቢትን እና አካባቢውን ሚሊሾች ስብሰባ ጠርተው ሴራ ሊሸርቡ ሲሉ ሴራው እንደከሸፈባቸው ተገልጧል። የብአዴን አመራሮች ያነሱትን ጥያቄ የአካባቢው ሚሊሾች አንድ በመሆን አጥብቀው በመቃዎማቸው ምክንያት ሊጭኑባቸው የነበረውን ተልኮ እና ሴራ ለመክሸፍ ችሏል ሲሉ ምንጮች በስልክ ተናግረዋል። አመራሮቹ በስብሰባው ውስጥ ፋኖን የማጥፋት አላማቸውን ሲያንፀባርቁ የተመለከቱ ሚንሾች ስለፋኖ የተነሱትን ሃሳቦች በሙሉ በአንድነት ተቃውመዋል። ታህሳስ 6/2015 ዓ/ም ማንፉድ የምትባል ቦታ ተነስቶ የነበረው ተኩስም የብአዴን አመራሮች ለወታደሮቻቸው የተሳሳተ መረጃ በመስጠት የፀጥታ ሃይሉንም ከፋኖ ጋር ለማጋጨት የሰሩት ሴራ መሆኑን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ በማሸበር ፋኖ ተደራጂቶ ሊዘርፍ እየመጣነው በማለት የጠነሰሱት ሴራ ነበር ሲሉ ተናግረዋል። ኦነግ ሸኔ በራችን ድረስ መጥቶ እየገደለን እንዴት ሃገር ጠባቂ የሆነውን ፋኖ እናሳድዳለን። ፋኖዎች እኮ ልጆቻችን ናቸው። ለምን ከልጆቻችን ጋር ታቃቅሩናላችሁ በማለት ስብሰባው ላይ ቁጣቸውን አሰምተዋል ተብሏል። አክለውም “እኛ ጠላታችን ኦነግ ነው፤ ማሳደድም፣ መደምሰስም ካለብን ኦነግን እንጂ ፋኖን አይደለም፤ ኦነግን ለመዋጋት ግን ዛሬም ነገም ፈቃደኞች ነን” ሲሉ ሃሳባቸውን አንፀባርቀዋል ሲሉ መረጃ ሰጭዎቹ ተናግራዋል። ሴራው ያልተሳካላቸው የብአዴን አመራሮች አንድ ቀን ተኩል የፈጀውን ስብሰባ በሽምግልና ይፈታል በማለት ስብሰባው መዘጋቱን ጨምረው ነግረውና። በመጨረሻም መረጃ ሰጭዎች በሽዋሮቢት በግፍ ታስረው ለሚገኙት የፋኖ አመራሮች ፍትህ እንጠይቃለን ፋኖዎቻችን ሃገር ጠባቂ እንጂ ወንጀለኛ አይደሉም በማለት መልክታቸውን አስተላልፈዋል። ዘገባው የአሻራ ሚዲያ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply