
#የብዓዴን/ብልፅግና ካድሬዎች ከላይኛው እስከ ታችኛው አመራር በተዋረድ የወረሱት አስነዋሪ ድርጊት! ለተፈናቃይ የተሰበሰበውን 84 ኩንታል ዕርዳታ የቀበሌ አመራሮች ሰርቀው ገዥ በማመቻቸት ወደ ታች ጋይንት ተጭኖ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተነገረ‼️ ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ በኩርብሃ ቀበሌ ለተፈናቃይ የተሰበሰበ በቆሎ ሌላ ቦታ ተጭኖ ሲንቀሳቀስ በህዝብ ክትትል ማስቆም መቻሉን የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት አሰታወቀ። የደቡብ አቸፈር ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀይሉ ጌታሁን እንደተናገሩት ለተፈናቃይ በሁሉም ቀበሌ እንዲሰበሰብ ተደርጎ በኩርብሃ ቀበሌ ከእያንዳንዱ አባወራና እማወራ 10 ኪሎ በቆሎ በኮሜቴ ተሰብስቦ 5 ኩንታል ተሰበሰበ ተብሎ ለወረዳ ሪፖርት ተደርጓል። ነገር ግን 84 ኩንታል የቀበሌ አመራሮችና የመንግስት ሰራተኞች ገዥ በማመቻቸት ወደ ታች ጋይንት ተጭኖ ሲንቀሳቀስ በህዝብ ርብርብ ግንቦት 23 ቀን 2015 ዓ/ም በመያዝ ወደ ቀበሌው በመመለስ ማህበራት እንዲገባ ሁኗል ። ወደ ማህበሩ ከገባ በኋላ የወረዳው መርማሪ ቡድን ቀበሌው ድረስ ወርዶ ምርመራ በማጣራት ለዞኑ አቃቢ ህግ መላኩን ገልፀዋል። መረጃው የደቡብ አቸፈር ኮምኒኬሽን ነው ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- Ashara Tv – https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng // https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post