የብድር አቅርቦት ችግር የንግድ ዘርፉን እየጎዳው ነው ተባለይህ የተባለው የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፉ ማህበራት ባዘጋጀው የብድር አቅርቦት ፋይዳ ለቢዝነሱ በሚል ርዕስ በተደረገ ውይይት…

የብድር አቅርቦት ችግር የንግድ ዘርፉን እየጎዳው ነው ተባለ

ይህ የተባለው የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፉ ማህበራት ባዘጋጀው የብድር አቅርቦት ፋይዳ ለቢዝነሱ በሚል ርዕስ በተደረገ ውይይት ነው።

የግል ዘርፉ በስፋት የሚቸገርበት የፋይናንስ አቅርቦት እጥረቱን ለመፍታት ብድሮችን ለግሉ ዘርፍ ማቅረብ ወሳኝ እንደሆነ በመድረኩ ተነስቷል፡፡

ብድሩን ለማግኘት በሚደረገው ሂደት ውስጥ ያሉት ቅድመ ሁኔታዎች ግን ውስብስብ እና ማስያዣዎቹ ምቹ አለመሆናቸው አንዱ ምክንያት እንደሆነ ተግልጿል።

የአዲስ ቻምበር ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ እንደተናገሩት፤ የግል ዘርፍን በፋይናንስ መደገፍ ወሳኝ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ይሁን እንጂ ለዘርፉ የሚቀርበው የብድር አቅርቦት በቂ እንዳልሆነ እና የቢዝነሱ ማህበረሰብ ብድሩን ለማግኘት የሚሄድበት እርቀት አስልቺ እና ውስብስብ መሆኑ ለዘርፉ ዋነኛ ችግር ነው ብለዋል።

በመድረኩ የተገኙት የፋይናንስ ተቋማት በጥናታቸው እንዳሳዩት ባንኮች የብድር ፖሊሲዎቻቸው አለመመቸት ለብድር ፈላጊው አለመሳካት አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል ፡፡

ተቋማቱ በጥናታቸው እንደገለፁት ተበዳሪው አካልም የሚበደረው በአይነት መሆኑ ለችግሩ አንዱ ምክንያት ነው ተጠቅሷል፡፡

ከብድር ጋር ተያይዞ የሚወጡት አዋጆች እና ፖሊሲዎቹም ሊፈተሹ እንደሚገቡ በመድረኩ ተነስቷል።

ለአለም አሰፋ
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሚያዝያ 03 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply