You are currently viewing የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር የፊታችን እሑድ መጋቢት 17 ቀን በመንበረ ጸባኦት ቅደስት ሥላሴ ካተድራል ይፈጸማል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር የፊታችን እሑድ መጋቢት 17 ቀን በመንበረ ጸባኦት ቅደስት ሥላሴ ካተድራል ይፈጸማል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ እና የብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) ሥርዓተ ቀብር የፊታችን እሑድ መጋቢት 17 ቀን በመንበረ ጸባኦት ቅደስት ሥላሴ ካተድራል ይፈጸማል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የብፁዕ አቡነ ባስልዮስ ክቡር አስከሬን ከሰሜን አሜሪካ ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ሀገር ቤት ገብቶ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እንደሚያርፍና የብፁዕ አቡነ አረጋዊ ዶ/ር ክቡር አስከሬንም በዚሁ ዕለት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም እንደሚገባ ተገልጿል፡፡ በማግስቱም ማለትም እሁድ መጋቢት 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከቅዳሴ በኋላ የሁለቱም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ክቡር አስከሬን በቅዱስ ፓትርያርኩ በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁም በሊቃውንትና በምዕመናን ታጅበው ወደመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ያመራሉ፡፡ በካቴድራሉም ዐውደ ምሕረት የሁለቱም አባቶች የሕይወት ታሪክ ከተነበበና በሊቃውንት መንፈሳዊ አገልግሎት ከቀረበ በኋላ ሥርዓተ ቀብራቸው እንደሚፈጸም የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ዶ/ር ስለሥርዓተ ቀብሩ መርሐ ግብር መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል ሲል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቪዥን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply