የብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

የብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

https://1.gravatar.com/avatar/7f09202441ad3b4b636e88820d6a7061?s=96&d=identicon&r=G

የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ሥርዐተ ቀብር ተፈጸመ፡፡

ብፁዕነታቸው፣ ሀገረ ስብከቱን በመምራት ላይ እያሉ ባደረባቸው ሕመም ከሓላፊነት ተገልለው እና በሕክምና ሲረዱ ቆይተው፣ ትላንት ኅዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም. በተወለዱ በ72 ዓመት ዕድሜያቸው ያረፉ ሲኾን፣ ዛሬ ጠዋት፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ሓላፊዎች፣ የገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ምእመናንና ወዳጆቻቸው በተገኙበት በተፈጸመው ሥርዓተ ቀብር፣ የብፁዕነታቸው ዜና ሕይወት እና ሥራ፣ በብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የሲዳማ እና ጌዲዮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በንባብ ተሰምቷል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም፣ “ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት አበርክተው በሕግ እና በሥርዓት ኖረው ወደ አምላካቸው ሔደዋል፤” በማለት የማጽናኛ ትምህርት እና ቡራኬ ሰጥተዋል፡፡

የብፁዕነታቸው በረከት ይድረሰን፤ አሜን፡፡

የዘገባ ምንጭ እና ፎቶዎች: ኢኦተቤ ቴቪ እና የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

Source: Link to the Post

Leave a Reply