የቦይንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ከስራቸው ሊለቁ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የቦይንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቭ ካልሁን በዚህ አመት መጨረሻ ከስራቸው እንደሚለቁ ኩባንያው አስታውቋል።

የቦይንግ ዋና ኃላፊው ጡረታ እንደሚወጡና ሊቀመንበሩ ለድጋሚ ምርጫ እንደማይቀርቡ ኩባንያው ነው ኩባንያው የገለፀው።

ኩባንያው በ2020 ዋና ሥራ አስፈፃሚውን ዴኒስ ሙይለን-በርግን ከሃላፊነታቸው በማንሳት ነበር ዴቭ ካልሁንን የተካው፡፡

የቀድሞ ዋና ሥራ አስፈፃሚው የተነሱት ኩባንያው በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ከደረሱት የ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋዎች በኋላ ያጋጠመውን ቀውስ ፈትቶ ወደ ስኬቱ እንዲመለስ ነው ተብሎ ነበር።

ከዚህ ቀደም በቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ላይ ያጋጠመውን የደህንነት ችግር ተከትሎ ኩባንያው ዛሬም ድረስ የደህንነት ቀውስ ገጥሞታል።

ምንም እንኳን ኩባንያው የአውሮፕላኖቹን ደህንነት እና የጥራት ቁጥጥር ደረጃዎቹን በአዲስ መልክ ክትትል እና ቁጥጥር በማድረግ ማሻሻያዎችን ቢያደርግም ዛሬም ድረስ የተለያዩ ምርምራዎች እየተደረጉበት ይገኛሉ።

በቅርቡ የአሜሪካው ግዙፉ የዘመናዊ አውሮፕላኖች አምራች ኩባንያ ድሪምላይነር አውሮፕላኖች የነበረባቸውን ጉድለቶች በተመለከተ ምሥጢር በማጋለጥ የሚታወቀው ጆን ባርኔት ከሰሞኑ መኪናው ውስጥ ሞቶ መገኘቱ ይታወሳል፡፡

በየውልሰው ገዝሙ

መጋቢት 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply