የቭላድሚር ፑቲንን  ተፎካካሪ ይሆናሉ የተባሉት ቦሪስ ንዴይዥዲን በሚቀጥለው ወር ከሚካሔደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይወዳደሩ በሩሲያ ምርጫ ኮሚሽን ታገዱ።በአንጻራዊነት ሩሲያ በዩክሬን ያደረገ…

የቭላድሚር ፑቲንን  ተፎካካሪ ይሆናሉ የተባሉት ቦሪስ ንዴይዥዲን በሚቀጥለው ወር ከሚካሔደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንዳይወዳደሩ በሩሲያ ምርጫ ኮሚሽን ታገዱ።

በአንጻራዊነት ሩሲያ በዩክሬን ያደረገችውን ወረራ ይቃወማሉ የተባሉት ንዴይዥዲን ለዕጩነት ለመወዳደር ባቀረቡት ማመልከቻ ከሰፈሩ ፊርማዎች 15 በመቶው ጉድለት ስላለባቸው መታገዳቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ቦሪስ ንዴይዥዲን ውሳኔውን ለመሞገት ፍላጎት ቢኖራቸውም ሙከራቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ውድቅ እንዳደረገው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።

የ60 ዓመቱ ፖለቲከኛ ጉዳዩን ለሩሲያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደሚያቀርቡ በማኅበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ባሰፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። በዕጩነት መመዝገብ እንደማይችሉ ከተረጋገጠ በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ይዋል ይደር እንጂ የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዝደንት እሆናለሁ” ሲሉም ተናግረዋል።

ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በሥልጣን የቆዩት ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ከመጋቢት 6 እስከ 8 ቀን 2016 በሚካሔደው ምርጫ ሌሎች ሦስት እጩዎች ይፎካከሯቸዋል።

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ግን ሦስቱም እጩዎች በፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ጽህፈት ቤት የሚደገፉ ሚናቸውም የትዕምርት የዘለለ እንዳልሆነ ዘግቧል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos
Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast
Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply