የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባህር ዳር፣ ወልዲያ፣ ደባርቅ፣ ወላይታ ሶዶ እና ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ፡፡

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ 5ሺህ 117 ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 623 ሴቶች ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 2 ሺህ 785 ተማሪዎችን አስመርቋል።

በተያያዘም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 773 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ አስመርቋል፡፡

በተጨማሪም የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ እንዲሁም የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ 5 ሺህ 310 ተማሪዎችን አስመርቀዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ተመራቂ ተማሪዎች በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ለምረቃ መብቃታቸው ለሌሎች ምሣሌ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

ተመራቂዎቹ ባገኙት እውቀት በታማኝነት ህዝቡን እንዲያገለግሉም ጥሪ አድርገዋል።

በብስራት መንግስቱ፣ አገኘሁ አበባው እና በጥላሁን ሁሴን

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን አስመረቁ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply