የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት ከቀኖና በተጨማሪ ኢትዮጵያዊ ባህልና እሴትን የሚጥስ በመሆኑ ተቀባይነት እንደማይኖረመውም አለች የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን እንደማትፈቀድና ቡራኬም እንደማትሰጥ አስታወቀች።

የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ባሳለፍነው ሰኞ የቤተ-ክርስትያኗ ካህናት ለተመሳሳይ ፆታ ጥንዶች ቡራኬ መስጠት እንዲችሉ ፈቃድ መስጠታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በጉዳዩ ላይ በሰጠችው መግለጫ፤ ቤተክርቲያኗ በየትኛውም መልክ ለተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን አትፈቅድም፤ አታጸድቅም፤ ጋብቻ ማለት በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚደረግ ህብረት ነው” ብላለች።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply