የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን በሱዳን ያሉ ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም ስደተኞቹ የት እንደገቡ አላውቅም አለ። አሻራ ሚዲያ ፤ ጳጉሜ 3/2013 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን…

የተመድ ስደተኞች ኮሚሽን በሱዳን ያሉ ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም ስደተኞቹ የት እንደገቡ አላውቅም አለ። አሻራ ሚዲያ ፤ ጳጉሜ 3/2013 ዓ.ም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) በሱዳን በሚገኙ ካምፖች ውስጥ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ቢቀንስም እነዚህ ስደተኞች የት እንዳሉ ግን አላውቅም ሲል ነው የገለጸው።… ድርጅቱ ይህን ያለው የኢትዮጵያ መንግሥት በሱዳን ለስደተኞች የሚሰጥ መታወቂያን የያዙ ግለሰቦች ከህወሓት ወገን ተሰልፈው እየተዋጉ ነው ማለቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ባወጣው መግለጫ ዩኤንኤችሲአር የሚሰጠውን የስደተኞች መለያ መታወቂያ የያዙ ታጣቂዎች ከሱዳን ድንበር ተሻግረው ወደ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል እንዲሁም ወደ አማራ ክልል ገብተዋል ሲል ወንጅሏል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ለዚሁ ምላሽ ባወጣው መግለጫም ከስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚወጡት ስደተኞች የት እንደሚሄዱ የሚያረጋግጥበት መንገድ እንደሌለው አስታውቋል። ባለፉት ጥቂት ወራት በሱዳን የስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር በተወሰነ ደረጃ እንደቀነሰ ገልጾ “ዩኤንኤችሲአር ወደ ትውልድ ሀገራቸው የተመለሱ ስደተኞችን ጨምሮ ከስደተኞች መጠለያ የወጡ ግለሰቦች የት እንዳሉ ማረጋገጥ አይችልም” ሲል ምላሽ ሰጥቷል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች የአይበገሬዎቹ ልሳን:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም :- https://t.me/asharamedia24 ዩትዩብ:- https://bit.ly/33XmKro

Source: Link to the Post

Leave a Reply