የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ ልዩ ስብሰባ ጠርቷል

የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት “በኢትዮጵያ ያለውን አሳሳቢ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ” ለመፍታት ዓርብ ታህሳስ 8 ልዩ ስብሰባ የሚያኬድ መሆኑን ገለጸ፡፡ ኢትዮጵያ ተቃውማለች፡፡

መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባው የተጠራው ታህሳስ 4 የአውሮፓ ህብረት በይፋ ያቀረበውን ጥያቄ መሠረት አድርጎ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የስብሰባውን መጠራት አስመልክቶ ታህሳስ አራት ባወጣው መግለጫ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጉዳይ የጠራው ስብሰባ ድርጅቱና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያደረጉት የጣምራ ምርምራና መንግሥት የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እያደረገ ያለውን ጥረት የገፋ መሆኑን አስታውቋል።

መንግሥት በመግለጫው በጥምር ሪፖርቱ የቀረቡ ምክር ሀሳቦችን ተቀብሎ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልጾ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአማራ እና አፋር ክልሎች የፈፀማቸውን አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ላይ ምርምራ ማድረግ ሲጠበቅበት በተወሰኑ ሃገራት የፖለቲካ ፍላጎት ምክንያት ያን አለማድረጉን አስታውቋል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply