የተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚከለክል መመሪያ እንደተዘጋጀ የሚዘዋወረው መረጃ ሀሰት ነው::

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 09፣ 2014 የተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚከለክል መመሪያ እንደተዘጋጀ የሚዘዋወረው መረጃ ሀሰት ነው:: የተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚከለክል መመሪያ እንደተዘጋጀ የሚዘዋወረው መረጃ ትክክል አለመሆኑን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ። ህጋዊ ፈቃድ የሌላቸው ታክሲዎች በተማሪዎች የሰርቪስ አገልግሎት በመሰማራታቸው በትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እየፈጠረ ይገኛል፡፡

ይህንንም ተከትሎ የትራንስፖርት እጥረቱ እንዳይባባስ መልእክት መተላለፉ ይታወሳል። በአንጻሩ መረጃውን እንደመነሻ በመውሰድ የተማሪዎች ሰርቪስ የሚሰጡ ታክሲዎች አገልግሎት እንዳይሰጡ የሚከለክል መመሪያ እንደተዘጋጀ ተደርጎ የሚዘዋወረው መረጃ ትክክል አለመሆኑን የትራንስፖርት ቢሮ ለአርትስ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ በቀጣይ በትራንስፖርት እጥረቱ ላይ የፈጠረውን አሉታዊ ተጽእኖ በመገምገም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ምክክር ተደርጎ ዝርዝር መረጃው የሚወጣ ይሆናል። በመሆኑም የተማሪዎች ሰርቪስ የተመለከተ አዲስ መመሪያ እስኪወጣ ከዚህ ቀደም አገልግሎቱን ሲሰጡ የነበሩ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው ታክሲዎች በነበሩበት ስራ ላይ እንዲሰማሩ ቢሮው መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply