ኢትዮጵያ በፖለቲካ ታሪክዋ የተረጋጋ ስርአት መመስረት ሳትችል ከ40 አመታት በላይ ዘልቃለች። በተለይ ደግሞ ኢሕአዴግ ከጫካ እስከ ከከተማ ባደረጋቸው ጦርነቶች እና ወደ ስልጣንም ከመጣ በኋለ ሰላማዊት ኢትዮጵያን ለመመስረት አልቻለም። በተለይ የሕወሓት አንጋፋ አባላት የሚባሉት እንደነ አቶ ስብሐት ነጋ አይነት ሰዎች እስከ ሕይወታቸው የመጨረሻ ጠርዝ ድረስ በጦርነቶች እና በግድያዎች ብሎም ከኔ ውጭ ማንም ወደ ስልጣን መምጣት የለበትም በሚል አባዜ ትግል ውስጥ ወቆየታቸው እነሱንም ሐገርንም ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል። ለመሆኑ ኢትዮጵያ የተረጋጋ ስርአት እንዴት ትመስርት የሚለው ጥያቄ አሁንም መመለስ አለበት። የሕወሓት አመራሮች በሰሜን እዝ ሰራዊት ላይ ከወሰዱት ግድያ ባሻገር በረጅም አመታት የአገዛዝ ዘመናቸው በተዘረጋው የመንግስት ስርአት ሰላማዊት ኢትዮጵያን ማምጣት እንደማይቻል ይነገራል። ከሕወሓት በሗላ ምን አይነት ኢትዮጵያ ትምጣ የሚለው መነጋገሪያ ጉዳይ ነው። በዛሬው ኢትዮጵያዊ ስንክሳራችን መጨረሻቸው ስላላማረው የሕወሓት ከፍተኛ አመራሮች ታሪካዊ ዳራ ይቃኛል።
ቀን 05/05/2013
አዘጋጅ፡ጥበቡ በለጠ
ኢትዮጵያዊ ስንክሳር
Source: Link to the Post