የተራራ ኔትወርክ አዘጋጅ ያሉበት እንደማይታወቅ ቤተሰቦቻቸው ገለጹ

“ተራራ ኔትወርክ” የተሰኘ የኢንተርኔት ላይ ሚዲያ አዘጋጅ ታምራት ነገራ በአዲስ አበባ ፖሊስ ከታሰረ አራት ቀናት ቢያልፉም የታሰረበትን ቦታ ፖሊስ ሊነገራቸው ፈቃደኛ አለመሆኑን ባለቤቱ ገለፁ።

ባለቤቱ ወይዘሮ ሰላም በላይ ፤ “ምክንያቱን ከምርመራ በኋላ እንነግራችኋለን ብለው አርብ ወደ ሦስተኛ ፖሊስ ጣብያ ቢወስዱትም የት እንደታሰረ ግን ማንም አልነገረንም” ብለዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን  “በወንጀል ድርጊት ተጠርጥሮ እንጂ በሙያው ምክንያት የታሰረ አንድም ጋዜጠኛ የለም” ሲል አስታውቋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

 

Source: Link to the Post

Leave a Reply