የተቃውሞ ሰልፍ በባህር ዳር

https://gdb.voanews.com/81d7843b-77f4-4fc0-842f-3a8e69d6e1cb_tv_w800_h450.jpg

ቁጥራቸው የበዛ መምህራንና ተማሪዎች የተሳተፉበት የተቃውሞ ሰልፍ ዛሬ በባህርዳር ከተማ ተካሂዷል።

“ዩናይትድ ስቴትስና ምዕራባዊያ በኢትዮጵያ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል” የሚሉት ሰልፈኞች ይህንኑ ተቃውሟቸውን በመፈክሮቻቸው አሰምተዋል።   

ሰሞኑን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ኢትዮጵያውያን በሚያደርጓቸው ሰልፎች የሚሰማው በእንግሊዝኛው ‘no more’ ወይም በአማርኛ “በቃ” የተሰኘው መሪ ቃል ዛሬም በባህር ዳሩ ሰልፍ ላይ ቀዳሚ ቃል ነበር።  

በሌላ በኩል በኢትዮጵያውያን የሚቀርቡትን እንዲህ ያሉ ቅሬታዎች የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አይቀበሉትም። ውሳኔዎቻቸው ከሰብዓዊ መብት መከበር ጋር የተያያዙ እንደሆኑ ይናገራሉ።  

Source: Link to the Post

Leave a Reply