የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በቅርቡ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የተፈፀመውን ጥቃት በፅኑ አውግዟል፡፡

የመንግሥታቱ ድርጅት የሥራ ኃላፊዎች በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የአሊንዳኦ ከተማ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎች በጦርነቱ መሰቃየታቸውንና መፈናቀላቸውን ገልፀዋል፡፡በዚያች ሀገር ማክሰኞች እለት ብቻ በተካሄደው ከባድ ውጊያ በሺ የሚቆጠሩ ሰዎችን ማፈናቀሉና የብዙዎችን ህይወት መቅጠፉ ተነግሯል፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪው ዴኒሥ ብራውን በሀገሪቱ የሰብዓዊ ድጋፉ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ገልፀዋል፡፡ለዚያ ምክንያቱ ደግሞ በሀገሪቱ ያለው አስከፊ የፀጥታ ሁኔታ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡

ሰሞኑን በአሊንዳኦ ከተማ በገበያ ላይ የነበሩ ንፁሃን ዜጎች በጠራራ ፀሐይ በታጣቂ ሃይሎች መገደላቸውን የዘገበው አናዶሉ ነው፡፡

ቀን 30/10/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply