የተባበሩት መንግስታት ለኢትዮጵያ ህይወት አድን ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ገለጸ፡፡የተባበሩት መንግስታት የምግብ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ እየከፋ ለመጣዉ የምግብ ዋስትና ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን አስታዉ…

የተባበሩት መንግስታት ለኢትዮጵያ ህይወት አድን ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን ገለጸ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የምግብ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ እየከፋ ለመጣዉ የምግብ ዋስትና ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተከሰተዉን ከፍተኛ ረሃብ ተከትሎ ህይወት አድን ድጋፎችን ለ3 ሚሊየን ዜጎች በመጪዎቹ ሶስት ሳምንታት ጊዜ ዉስጥ እንደሚያቀርብ ኤጀንሲዉ አስታዉቋል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም እስካሁን ድረስ በአፋር፣ አማራ፣ ትግራይ እና ሶማሌ ክልል ለከፍተኛ ረሃብ የተጋለጡ ወደ 6.2 ሚሊየን አከባቢ የሚደርሱ ዜጎችን መመዝገቡን በኢትዮጵያ የፕሮግራሙ ጊዜያዊ ዳይሬክተር ክሪስ ኒኮኢ ገልጸዋል፡፡

በታህሳስ ወር መጀመሪያ ላይ ተቋርጦ የነበረዉ የምግብ ድጋፍ መቀጠሉን ተከትሎ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ወደ 1.2 ሚሊየን ለሚጠጉ ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች ለሚኖሩ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ፕሮግራሙ በመጪዎቹ ሳምንታት 3 ሚሊየን ለሚጠጉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ዕቅድ የያዘ ሲሆን፤2 ሚሊየን የሚሆኑት በትግራይ የሚገኙ ዜጎች መሆናቸዉን ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ኤጀንሲዉ በአገሪቱ ያለዉን የተወሰነ የምግብ ክምችት ለመጨመር እና በበቂ ሁኔታ ድጋፍ ለማቅረብ 142 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገዉ አስታዉቋል፡፡

እስከዳር ግርማ
ጥር 29 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply