የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ለሚሰደዱ ተፈናቃዮች የበለጠ ድጋፍ እንዲደረግ አሳሰቡ ። የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነ…

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ለሚሰደዱ ተፈናቃዮች የበለጠ ድጋፍ እንዲደረግ አሳሰቡ ።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ለሱዳን ተፈናቃዮች አስቸኳይና ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግላቸዉ መጠየቃቸውን ኮሚሽኑ ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ኮሚሽነሩ በሶስት ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው፣ በሱዳን በተቀሰቀሰዉ ግጭት ምክንያት ወደ ኢትዮጵያ የገቡትን የሱዳን ስደተኞችን ለመርዳት የኢትዮጵያ መንግስት በUNHCR እና በአጋር ድርጅቶች ድጋፍ የሚያደርገውን ጥረት መመልከታቸውን መግለጫው አስታውቋል።

ኮሚሽነር ግራንዲ እንዳሉት  ከመጋቢት 2015 ጀምሮ ከ100ሺ በላይ ሰዎች ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፣ ከመካከላቸው ወደ 47ሺ የሚጠጉት ስደተኞችና ተገን ጠያቂዎች ናቸዉ። እነዚህስደተኞች ከመምጣታቸው አስቀድሞ በኢትዮጵያ 50ሺ ሱዳናውያን ስደተኞች ነበሩ።

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኘው በኩርሙክ ጊዘያዊ ማቆያ ዉስጥ የሚገኙ ከ20ሺ በላይ ስደተኞችና ተገን ጠያቂዎቹን ይዞታ መመልከታቸውን የተናገሩት ግራንዴ “ኢትዮጵያ ከሱዳን ለመጡት ተፈናቃዮች የምታደርገውን ልገሳ የሚያስመሰግን ብለውታል። ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ የላቀ ድጋፍ ሊደረግላት ይገባል ሲሉም አሳስበዋል።
ለጋሽ

ሃገሮች ተጨማሪ ድጋፍ ካላደረጉ ለተረጂዎች መድረስ እጅግ በጣም ከባድ ይሆናል” በማለት ግራንዲ ጥሪ አስትላልፈዋል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጥሪ አድርገዋል።

ጥር 22 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Source: Link to the Post

Leave a Reply