የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፤ የአዉሮፓ ህብረት፤ የአረብ ሊግ እና አሜሪካ የሱዳን ወታደራዊ ሃይል ስልጣኑን ለሲቪል መንግስት እንዲሰጥ ጠየቁየሱዳን ወታደራዊ ሃይል ጠቅላይ ሚኒስትሩን በቁጥጥ…

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፤ የአዉሮፓ ህብረት፤ የአረብ ሊግ እና አሜሪካ የሱዳን ወታደራዊ ሃይል ስልጣኑን ለሲቪል መንግስት እንዲሰጥ ጠየቁ

የሱዳን ወታደራዊ ሃይል ጠቅላይ ሚኒስትሩን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት ድርጅ፤ የአዉሮፓ ህብረት፤ የአረብ ሊግ እና አሜሪካ ሁኔታዉ እንዳሳሰባቸዉ በመግለጽ ላይ ናቸዉ፡፡

በሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ ተወካይ ቮልከር ፔርዝስ እንዳስታወቁት ፤ የጦር ሃይሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩንና ካቢኒያቸዉን ከአገተበት እንዲለቅ ጠይቀዋል፡፡

የአዉሮፓ ህብረት የዉጭ ጉዳዮች ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በበኩላቸዉ፤የሱዳን የሽግግር መንግስት ወደነበረበት እንዲመለስ እንጠይቃለን ነዉ ያሉት፡፡፡

በምስራቅ አፍሪካ የአሜሪካ ልዩ መልእክተኛ ጄፈሪ ፌልትማን በወታደራዊ ሃይሉ ድርጊት አሜሪካ እንዳዘነችና ህጋዊ አለመሆኑንም አስታዉቀዋል፡፡

ፌልት ማን ከትናንት በስተያ ወደ ካርቱም አቅንተዉ ከአገሪቱ ባለስልጣናት ጋር መምክራቸዉ ታዉቋል

የአረብ ሊግም እንዲሁ የሱዳን አለመረጋጋት እንዳሳሳበዉ መግለፁን አልጄዚራ ነዉ ያስነበበዉ፡፡

አብደላ ሀምዶክ ዛሬ ጠዋት ወታደራዊ ሃይሎች መኖሪያ ቤታቸዉን በመክበብ በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸው ይታወሳል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪም ሌሎች የካቢኔ አባላት የቤት እስረኛ ስለመሆናቸው ተሰምቷል።

በአሁኑ ሰዓት የካርቱም ጎዳናዎች በወታደሮች መዘጋታቸውም ታውቋል።

አባቱ መረቀ
ጥቅምት 15 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply