የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋዛ ያሉ ከ1ሺህ በላይ ነፍሰጡር እናቶች በከፍተኛ ደረጃ ለሞት የተጋለጡ ናቸዉ አለ፡፡

የተባበሩት መንግስታት በጋዛ ሰርጥ ያሉ 45ሺህ ነፍሰጡር እና ጡት የሚያጠቡ ሌሎች 68ሺህ እናቶች ለደም ማነስ፣ ለመድማት እና ለሞት በከፍተኛ ደረጃ የተጋለጡ ስለመሆናቸዉ አስጠንቅቋል፡፡

ድርጅቱ በጋዛ እየደረሰ ላለዉ የምግብ ዕጥረት የእስራኤል ያላቋረጠ ጥቃት ተጠያቂ ነዉ ያለ ሲሆን፤ በከፍተኛ ችግር ዉስጥ ላሉት ፍልስጤማዊያን ምግብ ለመድረስ የሚችለዉ አፋጣኝ የተኩስ አቁም ስምምነት ሲኖር ብቻ ነዉ ሲል ደምድሟል፡፡

በጥቅምት 7 በሃማስ እና በእስራኤል መካከል በተጀመረዉ ጦርነት ሴቶች እና ህጻናትን ጨምሮ ወደ 19ሺህ የሚሆኑ ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል፡፡

የተያዘዉ የፍልስጤም ግዛት ለ16 ዓመታት በእስራኤል ቁጥጥር ስር የቆየ ሲሆን፤ አሁንም ድረስ በቃል ሊገለጽ በማይችል ከባድ የሰብዓዊ ችግር ዉስጥ ነዉ ያለዉ ሲሉ የፍልስጤም እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር

በእስከዳር ግርማ

ታህሳስ 09 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply