የተባበሩት አማራ በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበር በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ወለህ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ 320 ሺህ ብር የሚገመት የአልሚ ምግብ ዱቄት ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲ…

የተባበሩት አማራ በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበር በዋግኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ወለህ ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ወደ 320 ሺህ ብር የሚገመት የአልሚ ምግብ ዱቄት ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 27 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የተባበሩት አማራ በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበር የቦርድ አባልና የሰብአዊ መብት ጉዳዮች አስተባባሪ አቶ አለልኝ ምህረቱ እንደተናገሩት ማህበሩ ከስዊድን አገር ከሚኖሩ ኢትጵያውያን ገንዘብ አሰባስቦ በማምጣት በተለያየ ምክንያት ለሚፈናቀሉ ወገኖች እርዳታ ይሰጣል። በዛሬው እለትም በዚህ መጠለያ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች 320 ሺህ ብር የሚገመት 100 ኩንታል የአልሚ ምግብ ዱቄት ድጋፍ ይዘን መጥተናል ብለዋል። በዚህ ዘመን እንዲህ በጣም የሚያሳዝኑ አባቶችን፣ እናቶችን እና ህፃናትን ከሞቀ ቤታቸው ተፈናቅለው ወጥተው ሲሰቃዩ ማየት በእጅጉ ያሳዝነኛል፡ ተፈናቃዮቹ ወደየመጡበት ቀየ ለመመለስ ካበቃቸው በተቻለው አቅም ማህበሩ እንዲቋቋሙ የማድረግ እቅድ አለው ያሉት አቶ አለልኝ ምህረቱ ይህንን ድጋፍ ሲሰጡ የመኪና ትብብርና የማስተባበር ስራውን ለአመቻቹላቸው የዋግ ልማት ማህበርን እና የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ተጠሪ ጽ/ቤትን በማህበሩ ስም አመስግነዋል። የዋግ ልማት ማህበር ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አምላኩ አበበ በበኩላቸው የህወሓት ወራሪ ቡድን በአካባቢያችን ላይ በፈፀመው ወረራ ምክንያት በጣም በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ተፈናቅለዋል። በአሁኑ ጊዜም እንደ ብሄረሰብ አስተዳደር የተፈናቃዮች ቁጥር ከ40 ሺህ በላይ ደርሷል። ይህ ተፈናቃይ የህብረተሰብ ክፍል በሦስት መጠለያዎች ይገኛል። ዛሬ ላይ የተባበሩት አማራ በጎ አድራጎት እና ልማት ማህበር ወለህ መጠለያ ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ላደረገልን ድጋፍ በተፈናቃይ ወገኖቻችን ስም ከልብ እያመሠገን እኛም ከማንኛውም በጎ አድራጊ ማህበር ጎን በመሆን የማስተባበር ስራችንን እንቀጥላለን በማለት ተናግረዋል ሲል ዋግ ኽምራ ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply