
በትግራይ ክልል ውስጥ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብር ቡድንነት ተሰይሞ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ፍረጃው ተነሳለት። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ መጋቢት 13/2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ላይ እንደወሰነው ህወሓት የአገሪቱ መንግሥት ሽብርተኛ ብሎ ከፈረጃቸው ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ እንዲወጣ ወስኗል። ይህ ውሳኔም ጦርነቱን ያስቆመው ስምምነት አንድ አካል እንደሆነ ይነገራል።
Source: Link to the Post