
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፓርላማ አባል የሆኑትን እና የቀድሞ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት የነበሩትን ዶ/ር ጫላ ዋታ ያለመከሰስ መብት አነሳ። የእንደራሴው ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ለምክር ቤቱ ጥያቄ የቀረበው ዛሬ መጋቢት 25/2015 ዓ.ም ሲሆን፣ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ ተወስኗል። ዶ/ር ጫላ ዋታ የቡሌ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ጊዜ የመንግሥት ግዢ ሥርዓትን ሳይከተሉ ግዢዎችን በመፈጸማቸው ነው የሕግ ከለላቸው የተነሳው።
Source: Link to the Post