የተወካዮች ም/ቤት የብድር መጠንን የሚያሳድገውን ህግ አጸደቀ

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የፓርቲ ልዩነት በተንጸባረቀበት መልኩ የዩናይትድ ስቴትስ የብድር መጠን ወደ 2.5 ትሪሊዮን ዶላር እንዲያድግ የሚያዘውን የህግ ረቂቅ ዛሬ ረቡዕ አጽድቆ ለፕሬዚዳንት ባይደን ፊርማ የመራው መሆኑ ተገለጸ፡፡ 

አገሪቱን ከእዳ ክፍያ ቀውስ ያድናታል የተባለው ረቂቅ ህጉ የጸደቀው 221 ለ209 መሆኑን የተነገረ ሲሆን፣ ቀደም ሲል በህግ መወሰኛው ምክር ቤት መጽደቁ ይታወሳል፡፡ 

ፕሬዚዳንት ባይደን በረቂቅ ህጉ ላይ ይፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሪፐብሊካንም ሆነ በዴሞክራት የአስተዳደር ዘመን፣ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት፣ ከገቢው በላይ የበዛ ወጭ እንዲኖረው የሚያስገድደውን የበጀት ህግ፣ ሲያጸድቅ የኖረ መሆኑም በዘገባው ተመልክቷል፡፡ 

የወጭና ገቢ ሚዛን በመዛባቱና የበጀት ጉድለት መፈጠሩ የብድር መጠንን ከጊዜ ወደዚያ እያደገ እንዲመጣ ያደረገው መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

ምክር ቤቱ የዩናይትድ ስቴትስ የመንግሥት የመበደር አቅም እንዲያድግ እኤአ ከ1960 ጀምሮ 80 ለሚሆን ጊዜ ማጽደቁ ተመልክቷል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply