የተወካዮች ም/ቤት የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ በጅት 768 ቢሊዮን ዶላር እንዲሆን ወሰነ

https://gdb.voanews.com/8e1715c8-5272-4310-96ea-e5f8b6e829a2_w800_h450.jpg

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት እኤአ ለ2022 የሚሆነው ወታደራዊ ወጭ 768 ቢሊዮን ዶላር እንዲሆን በትንናንትናው እለት ወስነዋል፡፡

360 ለ70 በሆነ ድምጽ የጸደቀው ወታደራዊ ወይም የመከላከያ በጀት ባልተመለደ መልኩ አነጋጋሪ ሆኖ መቆየቱ ተገልጿል፡፡ 

የሁለቱ ምክር ቤቶች መሪዎች በዝግ ስብሰባ ከተደረገ ውይይት በኋላ በ20 ዓመቱ የአፍጋኒስታን ቆይታ የደረሰውን ለመመርመር፣ የዩክሬንን ወታደራዊ ኃይል ለመደገፍ፣ ከቻይና ውጭ ሆና ራሷን ለማስተዳደር ለምትጥረው ታይዋን ድጋፍ ለመስጠት የሚውል የ300 ሚሊዮን ዶላር በጀት እንዲካተት መደረጉ ተመልክቷል፡፡ 

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያም በቻይና ሙስሊም ኡግሮች ጉልበት የተሰራውን ማንኛውንም የጦር መሳሪያ እንዳይገዛም በበጀት ህጉ ረቂቅ ክልከላው ተቀምጧል፡፡ 

የመጨረሻው በጀት ተወስኖ ሲለቀቅ ፕሬዚዳንት ባይደን ከጠየቁት በላይ 24 ቢሊዮን ዶላር ብልጫ እንዳለው ተነግሯል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply