የተዛቡ የሀሰት ትርክቶችን ለማስተካከል ምሁራን የሙያ ማህበር እንዲመሰርቱ መደረጉ  አሁን ለሚፈጠሩ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጥሩ ጅማሮ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በተለያየ መገናኛ ብዙኃን እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም አንድ አንድ ምሁራንና ፖለቲከኞች የሀሰት ትርክትን ፈጥሮ በመናገር አሁን ለሚታየው ማንነትን መሰረት ላደረገ ግጭትና ጥቃት ምክንያት ናቸው መባሉ ይታወሳል፡፡

በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ረዳት ፕሮፌሰርና የሰላም ሚኒስቴር አማካሪ ሳሙኤል ተፈራ እንደተናገሩት የሀሰት ትርክቶችን ለማስተካከል ምሁራን የጋራ መድረክ ፈጥረው እንዲነጋገሩ ማድረግ ተችሏል፡፡

በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የታሪክ ምሁራን በማሰባሰብ የተዛባ የሀሰት ትርክትን ለማስተካከል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመሆን  የሙያ ማህበር እንደሚመሰርቱና አንድ ወጥ የሆነ አቋም እንዲኖራቸው ስምምነት ላይ መደረሱንም ተናግረዋል፡፡

አሁን በመደራጀት ምዝገባ እያደረጉ መሆኑንን የተናገሩት ረዳት ፕሮፌሰሩ የሙያ ማህበር መመስረቱ በየቦታው የሚነሳውን ሀሰት ትርክት ለማስተካከል እንዲሁም ታሪክን አጉልቶ ወይም አጋኖ የሚናገሩትን ለማረቅና ለማስተካከል ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

የታሪክ ምሁራኑ ከተለያየ ብሄርና ሃይማኖት የተውጣጡ መሆናቸውን ገልጸው በሀሰት ትርክት የሚነሱ ግጭቶች ወደ ፊት የኢትዮጵያ ችግሮች ሳይሆኑ ልማትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ትኩረት ማድረግ እንድንችል ያደርገናል ብለዋል፡፡

ቀን 19/06/2013

አሐዱ ራድዮ 94.3

Source: Link to the Post

Leave a Reply