“የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንሰራለን” —-ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ ከመላው ኢትዮጵያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/Z-MlPzqPGuFMDfhQgALZf0aLrmRsJzv8ujoOeQzSnje0ykiBnPoD1o2yvMo-6YnsM9HGm3elLGwwSui5uX_q45ogi8LSg6vMop0DOt3NCYtCGkj_2hu-8WkFSKkZpBdQtGV-uJ8-aQAQ9Bwwrw1OEFah5XYUnSqLimNdE7QI7gYSGNOjxxD0l-m4l9adT5sX4d1Rjwv4qLhVxpyJcyHGtUiLfpnhbmAq1U1AssaGqpkUL5YJGmqIpabO_RBqwLbKUMitpmTLxkBQKPc1b1P6XJppNWCRBS-Eou0bwX-OhV0gt8POQCBEEXlgR8x4F_1rFlVW7EyPKCZr3SDho2kX6w.jpg

“የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ እንሰራለን” —-ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ

ከመላው ኢትዮጵያ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገልፀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት፤ ምክር ቤቱ ባካሄደው 28ኛ መደበኛ ስብሰባው ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ በሰጡት ወቅት ነው፡፡

ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎችና አስተያየቶች በሰጡት ምላሽና ማብራሪያ፤ መንግሥት በሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ከቀያቸው ለመመለስ በትኩረት እየሰራ መሆኑንና አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያስታወቁት፡፡

ባለፉት ዓመታት በበጎ አድራጊ ግለሰቦች ድጋፍ ከ60 ሺህ በላይ የአቅመ-ደካማ ቤቶችን በማፍረስና እንደገና በመገንባት ለነዋሪዎች መተላለፉን የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ፤ 5 ሺህ ለኪራይ የሚውሉ ቁጠባ ቤቶች ተገንብተው ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም አክለዋል፡፡

ሕገ-ወጥ የቤት ግንባታዎችን ለመከላከል ሁሉም አካላት ተረባርበው ማስቆም ካልተቻለ ችግሩ የከፋ ሊሆን እንደሚችል አስገንዝበው፤ በተለያዩ አካባቢዎች የሚገነቡ ሕገ-ወጥ ግንባታዎችን ለማስቆም ከሁሉም የክልል አስተዳደሮች ጋር ስምምነት መድረሱን ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/videos

Source: Link to the Post

Leave a Reply