የተፈጥሮ አደጋን ምክንያት አድርገው የዋጋ ጭማሬ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ክትትል በማድረግ እርምጃ እንደሚወስድ የሰሜን ወሎ ዞን አስጠነቀቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 16 ቀን 2…

የተፈጥሮ አደጋን ምክንያት አድርገው የዋጋ ጭማሬ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ክትትል በማድረግ እርምጃ እንደሚወስድ የሰሜን ወሎ ዞን አስጠነቀቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2…

የተፈጥሮ አደጋን ምክንያት አድርገው የዋጋ ጭማሬ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ ክትትል በማድረግ እርምጃ እንደሚወስድ የሰሜን ወሎ ዞን አስጠነቀቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 16 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሀገሪቱ አመዛኙ አካባቢ በተለይ ደግሞ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ፣ ኦሮሚያ ልዩ ዞን እንዲሁም ደቡብ እና ሰሜን ወሎ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ የገበሬውን ሰብል ክፉኛ አውድሟል። በተለይ በደቡብ ወሎ ወረባቦን ያየ ሌላ አንዳች አስረጅ ነገር አይፈልግም፤ ገበሬዎቹ በተስፋ ማጣት ውስጥ ሆነው አይናቸው እንባ ሲያቀር ላየ አንጀት ያላውሳል። በሰሜን ወሎ ሮቢት፣ ራያ ቆቦ አዲስ ቅኝት፣ ወርቄ፣ ገደመዩ አቧሬ፤ በሀብሩ ሀሮ እና ማምጋው አካባቢውን አዳርሶ ያስጎመጀውን የደጋሌት እና ጃምዮ ማሽላ እንዲሁም ማኛ ነጭ ጤፉን በአይን ብቻ እንዲቀር አድርጎታል። ይህን ተከትሎ በየከተሞቸ ባደረግነው ቅኝት ከሳምንት በፊት የምግብ እህል አቅርቦት በእጅጉ ቀንሶ የነበረ ሲሆን በዚህኛው ሳምንት ለእጥፍ የቀረበ የዋጋ ጭማሬ ተደርጎ በነጋዴው ሲቸበቸብ ውሏል። በተቃራኒው ገበሬ የመጭውን ርሀብ ፈርቶ የቤት እንስሳቶቹን ለገበያ ቢያቀርብም እጅግ ዝቅተኛ ዋጋ ተተምኖበታል። ለአብነት በወረባቦ አንድ ገበሬ 30 000 ብር የሚያወጣ በሬውን ገበያ አውጥቶ 17000 ተገምቶበት ሲመለስ ታዝበናል፤ ከወትሮው ዋጋ የማያወጣው ማሽላ ከናካቴው ጠፍቶ ከርሞ ያኔ ከ25 ብር በላይ ተሽጧል። በተመሳሳይ ሰሜን ወሎ ወልድያ ላይ ማክሰኞ ገበያ ጤፍ በጣሳ (1.1/4 ኪሎ) 50 ብር ይሸጥ የነበረው እስከ 75 ብር ተሽጧል፤ የከብት ተራው የበዓል ገበያ ይመስል ጢም ብል ሞልቷል፤ ይህም ገበሬው እንስሳቱን ለገበያ አውጥታል ማለት ነው። ድርጊቱን የኮነኑት አርሶ አደሮቹ የነጋዴዎቹን ስግብግብነት ነውር ሲሉ ገልጸውታል፤ ከአንበጣ መንጋው እኩልም ስጋት ደቅኖባቸዋል። የገበሬውን በሬ፣ ፍየል፣ በግ፣ ግመል …በርካሽ እየገዙ ከራሱ ገዝተው ያከማቹትን ጤፍ፣ ማሽላ፣ በቆሎ እና ሌሎች እህሎች እጥፍ እየጨመሩ ከመሸጥ በላይ የሚገዳደር ነውረኝነትና ስግብግብነትስ ከወዴት ይገኛል!? ይላሉ። ይህን ትዝብት ይዘን የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወልደ ተንሳይ መኮንን ያነጋገርን ሲሆን በሰሜን ወሎ ከ69 ሺህ በላይ አባወራ እና እማወራ ለችግር ስለመዳረጋቸውና እርዳታ እንደሚሹ ገልፀዋል። አሁን ላይ የክልሉ መንግስት የምግብ እህል ዱቄት ድጎማ ማድረግ መጀመሩን ገልጸው ይህን ጊዜ አብሮ ማለፍ ሲገባ በደላላ፣ ነጋዴዎች እና ያለአግባብ ለመክበር በሚፈልጉ ግለሰቦች ያለአግባብ ሐብት ማካበት ተገቢ አይደለም ብለዋል። ድርጊቱም አሳፋሪ ነው ያሉ ሲሆን አላግባብ ዋጋ በመጨመር በሚሸጡ ግለሰቦች እና ነጋዴዎች እንዲሁም በሚያከማቹ ግለሰቦች ላይ ከዛሬ ጀምሮ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ እርምጃ እንደሚወሰድ አቶ ወልደተንሳይ ገልፀዋል። አሁን ያለውን ሰብል በድጋሚ አንበጣ እንዳያወድመውና ያልተጠበቀ ዝናብ ሊኖር ስለሚችል ገበሬው ሰብሉን በጊዜ መሠብሠብ እንዳለበትም አሳስበዋል። ጋዜጠኛ አራጋው ሲሳይ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply